በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ አማካኝነት የተፈበረኩ ሀሰተኛ መረጃዎችም ለመለየት አዳጋች ሁነው መገኘታቸውን አንድ ጥናት አሳየ

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ሰኔ 23፣ 2015 ዓ.ም

  1. በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ አማካኝነት የተፈበረኩ ትዊቶች የመታመን ምጣኔያቸው በሰዎች ከተጻፉ ትዊቶች በልጦ መገኘቱን አንድ የጥናት ውጤት አሳየ። “AI model GPT-3 (dis)informs us better than humans” በሚል ርዕስ በሳይንስ አድቫንስስ (Science Advances) የምርምር መጽሔት በትናትናው ዕለት የታተመ ጥናት በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ አማካኝነት የተፈበረኩ ሀሰተኛ መረጃዎችም ለመለየት አዳጋች ሁነው መገኘታቸውንም አስነብቧል። ለጥናቱ በናሙናነት የቀረቡት ትዊቶች ቻትጂፒት-3 በተሰኘው ቴክኖሎጅ የተፈበረኩ መሆናቸውም ተገልጿል።
  1. የአውስትራሊያ መንግስት የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን በመቆጣጠር ረገድ ክፍተት የሚያሳዩ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የሚቀጣ አዲስ ረቂቅ ህግ ማዘጋጀቱን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ረቂቅ ህጉ ለአውስትራሊያ ኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ባለስልጣን የማስፈጸም ስልጣን የሰጠው ሲሆን ህጉን በሚተላለፉ ኩባንያዎች የሚሊዮን ዶላሮች ቅጣት ይጥላል ተብሏል። የሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነት ተሟጋቾች ረቂቅ ህጉ ጠበቅ ያለ መሆኑ እንዳሳሰባቸው ሲገልጹ ተስተውሏል።
  1. ሜታ በፌስቡክና በኢንስታግራም ፕላትፎርሞቹ ስለሚጠቀምባቸው የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅዎች ፍንጭ የሚሰጥ ማብራሪያ በትናንትናው ዕለት አጋርቷል። ማብራሪያው የተሰጠው የፕላትፎርሞቹ ደንበኞች ቴክኖሎጅዎች እንዴት እንደሚሰሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታስቦ መሆኑ ተገልጿል። በማብራሪያው ከተካተቱት መካከል የጓደኝነት ጥቆማ፣ በኒውስ ፊድ የይዘቶች ምርጫና ቅደም ተከተል፣ ኖቲፊኬሽን ወዘተ እንዴት እንደሚከወኑ የሚገልጹ ይገኙበታል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን በግል የመረጃ መለዋወጫ መተግበሪያዎች ስለሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች የሚብራራ ጽሁፍ በአፋን ኦሮሞ አድርሰናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2054

– የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢድ አል አረፋ በአልን በማስመልከት ስጦታና ሽልማት አዘጋጅቷል ተብለው የተሰራጩ ማጭበርበርያዎች የተመለከተ መልዕክት አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2057

-በማህበራዊ ሚዲያ መረጃ አወሳሰዳችን ላይ ተጽኖ ስለሚያሳድሩ ጉዳዩች የሚተነትን ጽሁፍ በትግረኛ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2059

-ስለ አማተር የመረጃ አጣሪነት ገለጻ የሚያደርግ ጽሁፍም አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2061

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::