እጃቸውን የሰጡ የኤርትራ ወታደሮችን ያሳያል ተብለው የተለቀቁት ምስሎች የተሳሳቱ ናቸው

የካቲት 27፣ 2018
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከህወሓት አመራሮች ጋር ከሰሞኑ ያደረጉትን ውይይት ያሳያል በሚል እየተጋራ ያለው ቪዲዮ የቆየ ነው
/ኢትዮጵያ ቼክ/- በርካታ የፌስቡክ እና የኤክስ (የቀድሞ ትዊተር) አካውንቶች ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከሰሞኑ ከህወሓት አመራሮች ጋር ውይይት አደረጉ በሚል በስክሪን ቅጂዉ ላይ የሚታየዉን ቪዲዮ እያጋሩ ይገኛሉ።
በዚህ ቪዲዮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)፣ የቀድሞ እና የአሁን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንቶች አቶ ጌታቸዉ ረዳ እና ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም ሌሎች የፌደራል መንግስት እና የህወሓት አመራሮች ሰላምታ ሲለዋወጡ እና ሲወያዩ ይታያሉ።
ይህን ቪዲዮ በሰበር መረጃ መልኩ ካጋሩ የኤክስ ተጠቃሚዎች መካከል ‘Habtish Gurmu (Commentary)’ የሚል ስም ያለው አካዉንት ይገኝበታል።
ይህ አካዉንት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት በተመለከተ ከህወሓት አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸዉን ያሳያል ያለውን ቪዲዮ አጋርቷል።
በተጨማሪም “ይህን ግብ ከማሳካት ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ትግራይ ክልል እንዲገባ ህወሓት ተስማምቷል” የሚል መረጃም አካቷል።
ይህን በጽሁፍ እና ቪዲዮ የቀረበ መረጃ ከ50 በላይ የኤክስ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን በርከት ያሉ ሀሳቦችም ተሰጥተዉበታል።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በቪዲዮው ላይ ባደረገዉ ማጣራት ቪዲዮው ሁለቱ አካላት “ሰሞኑን አደረጉ” ተባለን ውይይት እንደማያሳይ አረጋግጧል።
ቪዲዮው ከአመት በፊት ህዳር 26/2017 ዓ.ም የተደረገን ውይይት የሚያሳይ ሲሆን በወቅቱም የትግራይ ክልልን የጸጥታና የፖለቲካ አስተዳደር በተመለከተ ከትግራይ ክልል የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር የተደረገ ውይይት እንደሆነ በሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን ተዘግቦ ነበር።
ለማሳያ ያክል ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን (FMC) ውይይቱን በተመለከተ በወቅቱ በፌስቡክ ገጹ አጋርቶት የነበረዉ ዘገባ በዚህ ማስፈንጠሪያ ይገኛል፡ https://www.facebook.com/share/v/1HjEfnK5t7/?mibextid=wwXIfr እና https://www.facebook.com/share/18BxuFFoU2/?mibextid=wwXIfr
በሌላ በኩል የፌደራል መንግስት እና ህወሓት አንዱ ሌላኛዉን ወገን ‘ለጦርነት እየተዘጋጀ’ ነው በሚል በተደጋጋሚ ሲካሰሱ የሚደመጥ ሲሆን ይህም በድጋሚ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።
ኢትዮጵያ ቼክ
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::





