የአርሰናል ደጋፊዎች ‘የዶ/ር ዐቢይ ታማኝ ደጋፊ ነን’ የሚል መልዕክት የያዘ ባነር ይዘዉ የተነሱት ፎቶ በሚል እየተጋራ የሚገኝ ምስል በቅንብር የተሰራ ነው

ሰኔ 2፣ 2018
/ኢትዮጵያ ቼክ/- በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በርካታ ተከታዮች ባሏቸው ገጾች እና ግለሰቦች ዘንድ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው “በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል” ብለዋል የሚል ጽሁፍ (Caption) የተለጠፈበት ምስል በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።
ይህ እየተሰራጨ ያለው ምስል የፎቶ ማቀናበሪያ መተግበሪያዎችን በመጠቀም የተቀነባበረ እና ሀሰተኛ መረጃን ለማስተላለፍ ሆን ተብሎ የተሰራ መሆኑን አረጋግጠናል።
ትክክለኛው እና ያልተቆረጠው ምስል የተወሰደው የገቢዎች ሚኒስቴር ሚያዚያ 01 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ካጋራው መረጃ ላይ ነው።
ዋናው መረጃ የሚያወራው የዩናይትድ ኪንግደም የግብር፣ የክፍያ እና የጉምሩክ ባለሥልጣን (HMRC) በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሲያካሂደው የነበረውን የታክስ ትራንፎርሜሽን ፕሮግራም ድጋፍ (Tax Transformation Program) ማጠናቀቁን በሚመለከት ነው (ሊንክ: https://www.facebook.com/share/p/1A2mhcT8s1/)
በዚህ መድረክ ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ ተገኝተው ውይይት ያደረጉ ሲሆን የተሰራጨው ሀሰተኛ ምስል ከዚሁ እውነተኛ የፎቶ ስብስብ ላይ ተቆርጦ የተወሰደ ነው።
ቅንብሩን የሰሩት አካላይ ይህንን ትክክለኛ ምስል በመውሰድ፣ የቴሌቪዥን ዜና እይታውን ትክክለኛ በማስመሰል እና ከስሩ “በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል” የሚል የሀሰት የሆነ ጽሁፍ በማስገባት አሰራጭተውታል።
ማህበረሰቡ ይህ ምስል የተጭበረበረ እና ከእውነተኛ መረጃ ላይ ተቆርጦ የተወሰደ መሆኑን ተገንዝቦ እንዲህ አይነቱን ሀሰተኛ መረጃ ከማመን እና ከማጋራት እንዲቆጠብ ኢትዮጵያ ቼክ ይመክራል።
ኢትዮጵያ ቼክ!
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::





