ሰሞኑን በአማራ ክልል ዋድላ ወረዳ የተገለበጠ የመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪን ያሳያል በሚል እየተጋራ ያለው ምስል የቆየ ነው

ሰሞኑን በአማራ ክልል ዋድላ ወረዳ የተገለበጠ የመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪን ያሳያል በሚል እየተጋራ ያለው ምስል የቆየ ነው

ህዳር 19፣ 2018

ይህ በስክሪን ቅጂዉ (screenshot) ላይ የሚታይ የጦር ተሽከርካሪ ሰሞኑን በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ የተገለበጠ የመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪ እንደሆነ የሚጠቁሙ መረጃዎች እየተጋሩ ይገኛሉ።

መረጃዉን ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘Dereje Habtewold’ የሚል ስም እና ከ240 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል።

ገጹ “የፋኖን ጥቃት ለማምለጥ በፍጥነት ሲያሸከረክር የነበረ ኦራል መኪና” በማለት የገለጸው ተሽከርካሪ በዋድላ ወረዳ “የዶጌት ሚካኤል” የሚባል ቦታ እንደተገለበጠ ጠቅሷል።

በተመሳሳይ መልኩ ከ140 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እና ‘Amhara Today’ የሚል ስም ያለዉ የፌስቡክ ገጽም ምስሉን እና መረጃዉን አጋርቷል። በዚህ ገጽ የተጋራዉን መረጃም ከ60 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰዉ ያጋሩት ሲሆን ከ200 በላይ አስተያየቶች ተሰጥተዉበታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገዉ ማጣራት ምስሉ ሰሞኑን በአማራ ክልል ዋድላ ወረዳ የተገለበጠ የመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪን እንደማያሳይ አረጋግጧል።

የጉግል ምስልን በምልሰት መፈለጊያ (Google Reverse Image Search) በመጠቀም ባደረግነዉ ማጣራት ምስሉ ከ3 ዓመታት በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጋርቶ እንደነበር ተመልክተናል።

በወቅቱ የተሽከርካሪዉን ምስል ያጋሩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች የጦር ተሽከርካሪዉ የትግራይ ሰራዊት ሲጠቀሙበት የነበረ ተሽከርካሪ እንደሆነ በመጥቀስ ምስሉን አጋርተው ነበር፡ https://www.facebook.com/share/1H4iXfQULT/?mibextid=wwXIfr

ከሌላ ቦታ ተወስደዉ ከአዉድ ውጭ በሆነ መልኩ የሚጋሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::