እነዚህ ምስሎች የኤርትራ አየር ሃይል በትላንትናው እለት በአስመራ ‘ያደረገውን የአየር ትርዒት’ አያሳዩም!

ግንቦት 18፣ 2017
በርከት ያሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እነዚህን ምስሎች “የኤርትራ አየር ሃይል ትላንት እሁድ ግንቦት 17፣ 2017 ያደረገውን የአየር ትርዒት ያሳያሉ” በሚል ማጋራታቸውን ተመልክተናል።
ምስሎቹን እየሻከረ እንደመጣ ከሚነገርለት የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ጋር በማገናኘት ያጋሩም አሉ።
በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኤርትራውያን 34ኛውን የኤርትራ ነጻነት በዓል በትላንትናው እለት ያከበሩ ሲሆን በኤርትራ ደግሞ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ የሀገሪቱ የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮች በተገኙበት ተከብሯል።
የአስመራዉ አከባበር በተለያዩ ትርዒቶች የታጀበ ቢሆንም “የሀገሪቱ አየር ሃይል ያደረገውን የአየር ትርዒት ያሳያሉ” በሚል የተጋሩት ምስሎች ግን ትክክለኛ እንዳልሆኑ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።
በዚሁ መሰረት ምስልን በምልሰት መፈለጊያ መገልገያዎችን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ከአመታት በፊት የተነሱ መሆናቸውን ተመልክተናል።
ምስሎቹ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ ሲጋሩ የቆዩ ሲሆን አንዳንዶቹ ከ15 አመታት በፊት የተነሱ ናቸው።
እኚህ “የኤርትራ አየር ሃይል በትላንትናው እለት ያደረገውን የአየር ትርዒት ያሳያሉ” በሚል የተጋሩትን ምስሎች ከአመታት በፊታ ካጋሩ ድረ-ገጾች መካከል የተወሰኑት ቀጥሎ ባሉት ማስፈንጠሪያዎች ይገኛሉ። ማስፈንጠሪያዎችን በመጫንም ከአመታት በፊት የተጋሩ ምስሎቹን መመልከት ይቻላል፡
https://www.globalsecurity.org/military/world/russia/mig-29-pics.htm
https://www.facebook.com/share/1EL5fvEHrK/
http://www.madote.com/2010/02/pictures-of-eritrean-air-force.html
የቆዩና ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛና የተሳሳቱ መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።
ኢትዮጵያ ቼክ
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
