የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

መስከረም 10፣ 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፍርድ ቤት ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር አሰራጭተዋል ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ እንደቀጣቸው የወረዳው ፖሊስ በሳምንቱ አጋማሽ አስታውቋል። አንደኛ ተከሳሽ ተመስገን ፍቅሩ በአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስራት እና የ2,000 ብር መቀጮ እንደተበየነበት የተገለጸ ሲሆን ሁለተኛ ተከሳሽ እንርያስ ባሎ ላይ የአንድ ዓመት ጽኑ እስራት እንደተፈረደበት የወረዳው ፖሊስ በፌስቡክ ገጹ አስነብቧል። ያሰራጩትን መረጃ በተመለከተ ምንም የተባለ ነገር የለም።

2. ኬንያ የሰውሰራሽ አስተውሎት መገልገያዎችን ላልተገባ አላማ በማዋል ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን የሚፈበረኩ አካላትን ለመቆጣጠር ያለመ ህግ ለማውጣት በሂደት ላይ መሆኗን ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ መግለጻቸውን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ፕሬዝደንት ሩቶ ይህን የገለጹት በመንግስት ግልጸኝነት ላይ በሚመክር አንድ ፓነል ላይ በተገኙበት ወቅት ሲሆን ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ከዲሞክራሲ ስርዐት አንጻር የደቀነውን ስጋት ኣአጽኖት ሰጠውታል።

3. ሜታ ፕላትፎርሞቹን በመጠቀም ሀሠተኛ መረጃን በማሰራጨትና ያልተገባ ተጽኖ በመፍጠር የፈረጃቸውን የሩስያ መንግስት የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትን ገጾች መዝጋቱን አስታውቋል። ከተዘጉት የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትን ገጾች መካከል የአርቲ እና የሮሽያ ሴጎኛ እንደሚገኙበት ተገልጿል። ሜታ እርምጃውን ከመውሰዱ በፊት ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትልና ምርመራ ማድረጉን አስነብቧል። በዩክሬንና በሩሲያ መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ ሜታና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭዎች ተመሳስይ እርምጃዎችን ሲወስዱ መቆየታቸው ይታወቃል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥

-ለሀሠተኛ መረጃ የሚያጋልጡንን አስቻይ ሁኔታዎች የሚያስረዳ ጽሁፍ አፋን ኦሮሞ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2449

-የቀድሞውን የመከላከያ ሚንስትር ለማ መገርሳን በተመለከተ የተሰራጨን መረጃ አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2450

-እርዳታ አድርጉልን በሚል ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚንቀሳቀሱ አጭበርባሪዎችን የተመለከተ ማስጠንቀቂያ አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2451

-የሰውሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም በድምጽ ስለሚሰሩ የማጭበርር መንገዶች የሚያስረዳ ጽሁፍ በትግርኛ አቅርበናል:

-ሪፖርት በማድረግ የጥላቻ ንግግሮችን ስርጭት መቀነስ የምንችልበትን አግባብ የሚያሳይ መልዕክትም አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2452

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::