ይህ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ እንደተወሰደ ተደርጎ የተሰራ የስክሪን ቅጅ ሀሠተኛ ነው

መስከረም 02፣ 2017 ዓ.ም
ባሳለፍነው ሰኞ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ እንደተወሰደ ተደርጎ የተሰራ የስክሪን ቅጅ ሲዘዋወር ተመልክተናል።
በስክሪን ቅጅው ላይ “እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ እያልን 12ኛ ክፍል የወደቃቹ ጓዶች በአስቸኳይ ዋናው መስሪያ ቤታች ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን” የሚል ጽሁፍ ይነበባል።
ይህ የስክሪን ቅጅ በፌስቡክ፣ በኤክስ እና በቲክቶክ በስፋት መጋራቱንም አስተውለናል።
እውነት የመሰላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ስለመኖራቸው የአስተያየት መስጫ ሳጥኖችን በማንበብ ታዝበናል።
ሆኖም ይህ የስክሪን ቅጅ ከኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ አለመሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።
ይህንንም ወደ ኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ በማምራት ማወቅ ይቻላል።
ትክክለኛውን የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ ይህን ማፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል:
https://www.facebook.com/fdredefense.official?mibextid=ZbWKwL
ሆን ተብለው እና ተቀናብረው የሚለቀቁ የስክሪን ቅጅዎችን ሳናረጋግጥ ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
