የጋና የሰላም ምክር ቤት የጥላቻ ንግግር በሀገሪቱ ሰላምና ደህንነት ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት እንደገባው አስታወቀ

The Ghana Peace Council is concerned that hate speech may cause problems for the peace and security of the country.

ጳጉሜን 01፣ 2016 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

  1. የጋና ብሔራዊ የሰላም ምክር ቤት እየተባባሰ የመጣው የጥላቻ ንግግር በሀገሪቱ ሰላምና ደህንነት ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት እንደገባው አስታወቋል። ምክር ቤቱ በፖለቲካ ተቀናቃኞች መካከል የሚታየው የጥላቻ ንግግር ለከት ካልተበጀለት በመጭው ታህሳስ ወር መጀመሪያ ከሚደረገው ምርጫ በፊት የሰላም መደፍረስ ሊከስት ይችላል የሚል ስጋቱን ገልጿል።
  1. በፈረንሳይ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው የቴሌግራም መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፓቬል ዱሮቭ ፕላተፎርሙ የወንጀለኞችና የምግባረ ብልሹዋች መናህሪያ ሆኗል ተብሎ የቀረበበትን ክስ አስተባብሏል። ዋና ስራ አስፈጻሚው ከሰዐታት በፊት ባስነበበው ረዘም ያለ ምላሽ ቴሌግራም በየቀኑ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ህግ ጣሽ አካውንቶችና ቻናሎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው ሲል ገልጿል። ክትትልና ቁጥጥርን በተመለከተ ደግሞ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅርበት እንደሚሰራ የገለጸው ዱሮቭ በዚህ እረገድ የተሻለ ስራ ለመስራት መዘጋጀቱንም አስነብቧል።
  1. አንድ የብራዚል ፍርድቤት ኤክስ ትዊተር በሀገሪቱ ኣአገልግሎት ላይ እንዳይውል እግድ መጣሉን አለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ፍርድቤቱ እግዱን የጣላው ኤክስ በብራዚል የህግ ተወካይ አላስቀመጠም በሚል መሆኑ ተጠቅሷል። በብራዚል ህግ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭዎች በሀገሪቱ ቋሚ የህግ ተወካይ እንዲኖራቸው ያስገድ ዳል። የፍርድቤቱን እግድ ተላልፎ ቪፒኤንም እና ስታርሊንክ በመጠቀም ጨምሮ ኤክስን በማንኛውም መንገድ የተገለገለ ሰው በቀን እስከ 9000 የአሜሪካ ዶላር ይቀጣል ተብሏል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥

-በፋኖ ታጣቂዎች የተማረኩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን ያሳያል የተባለን ፎቶ አጣርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2434

-ሀሰተኛ መረጃን እንድናምን ሊያደርጉ ሰልሚችሉ ስነልቦናዊ ጉዳዮች የሚያብራራ ጽሁፍ በትግርኛ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2435

-አሜሪካ ተራድኦ ድርጅት እንደተፃፈ ተደርጎ እየተሰራጨ የሚገኝ ደብዳቤንም ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2436

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::