በአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ዙርያ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ስለተሰራጨው መረጃ መንግስት ምን ምላሽ ሰጠ?

Ethiopia church demolishing issue

ነሐሴ 7፣ 2016 ዓ.ም

ከሰሞኑ የአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ከኮሪደር ስራ ጋር በተያያዘ ሊፈርስ እንደሆነ በርካታ መረጃዎች ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲተላለፉ ነበር።

እነዚህ መረጃዎች የቤተክርስቲያኒቱን ይዞታ ለሌላ ቤተ እምነት ሊሰጥ እንደሆነ ጠቅሰው መፍትሄ እንዲሰጥ ሲጠይቁ ነበር።

ይሁንና የቂርቆስ ኮሚኒኬሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከአፍሪካ ህብረት ጫፍ እስከ ቡልጋሪያ በሚከናወነው የኮሪደር ልማት የተነሳ የአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሊፈርስ ነው እየተባለ የተናፈሰው መረጃ የተሳሳተ ነው ብሏል።

ተቋሙ “ቤተክርስቲያኗ ላይ የሚፈፀም የተለየ ነገር አይኖርም” በማለት የሀይማኖት አባቶች ምዕመናኑን እንዲያረጋጉ ጠይቀዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ መረጃውን ሰጠ የተባለው የቂርቆሰ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሰላም እና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ስዩም መኮንን በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክፍለ ከተማው አስተዳደር አስታውቋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::