የትምህርት ሚኒስቴርን ስምና አርማ በመጠቀም ተዘጋጅቶ እየተጋራ የሚገኝ ይህ ደብዳቤ ትክክለኛ አይደለም

ሐምሌ 10፣ 2016 ዓ.ም
ይህ ምስሉ የሚታየው ደብዳቤ ከትምህርት ሚኒስቴር ለባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ እንደተፃፈ ተደርጎ በመዘጋጀት በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተጋራ አንደሚገኝ ተመልክተናል።
በምስሉ እንደሚታየው “ደብዳቤው” ሐምሌ 06፣ 2016 እንደተፃፈና ጉዳዩም የአንደኛ አመት ተማሪዎች የትምህርት መስክ (ዲፓርትመንት) ምደባን እንደሚመለከት ተጠቅሷል።
በዚሁ መሰረት አዲስ ገቢ ተማሪዎች ውጤት አያያዝ እንዴት መሆን እንዳለበት “በደብዳቤው” ተዘርዝሯል።
የዚህን ደብዳቤ ትክክለኛነት እንድናጣራ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታዮችም ጥቆማ የሰጡን ሲሆን እኛም የትምህርት ሚንሰትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን መረጃ ጠይቀናል።
እርሳቸውም ይህ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተጋራ የሚገኝ ደብዳቤ ሀሰተኛ መሆኑን ነግረውናል።
በተጨማሪም የደብዳቤው ይዘት ላይ ባደረግነው የፎቶፎረንሲክስ ምልከታ በርካታ አጠራጣሪና የተነካኩ ይዘቶች መኖራቸውን ተመልክተናል።
በቅንብር ተሰርተው ማህበራዊ ሚድያ ላይ ከሚቀርቡ ሀሰተኛ የፅሁፍ፣ የምስል፣ የድምፅ እንዲሁም የቪድዮ መረጃዎች ራሳችንን እንጠብቅ።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
