የጫካ ፕሮጀክትን ያሳያል በሚል በሚድያዎች እየተጋራ የሚገኘው ምስል በካንኩን፣ ሜክሲኮ ሊሰራ የታቀደ ፕሮጀክት ነው

ሰኔ 05፣ 2016 ዓ.ም
ተያይዞ የሚታየዉ ምስል መንግስት በየካ ተራሮች ላይ እያስገነባዉ የሚገኘዉ የጫካ ፕሮጀክትን የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ በተለይ የመንግስት ሚድያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ።
ፕሮጀክቱ ቤተመንግስትን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በዉስጡ የያዘ ሳተላይት ከተማ (satellite city) እንደሆነ የተነገረለት ነዉ።
ይሁን እንጂ ይህ ምስሉ የሚታየዉ ንድፈ-ሀሳብ በጣሊያናዊዉ አርክቴክት ስቴፋኖ ቦኤሪ የተሰራ ሲሆን በሜክሲኮ ካንኩን ከተማ ለመሰራት የታሰበ ዘመናዊ ከተማ ነው። ማስረጃ: https://transsolar.com/projects/smart-forest-city-cancun-masterplan-boeri
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የዛሬ ሁለት አመት ገደማ በተካሄደ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉባዔ ላይ በየካ ተራሮች ላይ እየተገነባ የሚገኘው ፕሮጀክት ዘመናዊ እና ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካም ኩራት የሚሆን እንደሚሆን ተናግረዉ ነበር፣ ፕሮጀክቱም ከ 400 እስከ 500 ቢልየን ብር የሚፈጅ እንደሆነም ገልፀው ነበር።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
