ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዝጋቷ ምክንያት 144.8 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘት የምትችለውን ገቢ ማጣቷ ተገለጸ

The Ghana Peace Council is concerned that hate speech may cause problems for the peace and security of the country.

ሰኔ 30፣ 2015

  1. ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዝጋቷ ምክንያት እአአ ከየካቲት 9 ጀምሮ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ባሉት ጊዜያት ብቻ 144.8 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘት የምትችለውን ገቢ ማጣቷ ተገለጸ። ይህን ስሌት ይፋ ያደረገው የኢንተርኔት መዘጋት በኢኮኖሚ ላይ ያለውን ተጽኖ የሚያጠናው የኢንተርኔት ሶሳይቲ (Internet Society) መሆኑን ሳምንታዊው ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል። በኢትዮጵያ ከመጋቢት 2015 ዓ.ም ጀምሮ በፌስቡክ፣ በዩቱብ፣ በቲክቶክ እና በቴሌግራም የማህበራዊ ሚድያ አገልግሎት ሰጭ መተግበሪያዎች ላይ ዕቀባ መጣሉ ይታወቃል።
  1. ሜታ ትዊተርን ይቀናቀናል የተባለ አዲስ የማህበራዊ ሚዲያ በትናትናው ዕለት ይፋ አድርጓል። ይህ “ትሬድ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲሱ የማህበራዊ ሚዲያ ከኢንስታግራም ጋር የተቆራኘ መሆኑን ተመልክተናል። የሜታ መስራች ማርክ ዙከምበርግ ትሬድ የሀሳብ መድረክ ሆኖ የማገልገል ተልዕኮ እንዳለውም ገልጿል። በሌላ በኩል የትዊተር ባለቤት ኢሎን መስክ ሜታን የንግድ ሚስጥሮችንና የአእምሯዊ ፈጠራ መብቶችን በመመተፍ እንደሚከስ በጠበቃው በኩል አስታውቋል።
  1. የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኦንላይን የሚፈጸምን የጥላቻ መልዕክት ለመከላከል እና መፍትሄ ለመፈለግ ያስችላል ያለው አዲስ የፖሊሲ ሰንድ በሳምንቱ አጋማሽ ይፋ አድርጓል። የተመድ የዘር ማጥፋት ቢሮ የዘር ማጥፋት ተከላካይ ቢሮ ይፋ ያደረገው ይህ የፖሊሲ ሰንድ በአለም አቀፍ እንዲሁም በሀገራት ውስጥ በኦንላይን የሚፈጸምን የጥላቻ መልዕክት ለመከላከል እና መፍትሄ ለመፈለግ አይነተኛ መሳሪያ ሊሆን ይችላል ተብል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን ሀሠተኛ መረጃን ለመለየት ስለሚረዱ የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅዎች ጽሁፍ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2066

-በአርቲስት ቴውድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ ስም የተከፈተን ሀሠተኛ የቲክቶክ አካውንትንም አጋልጠናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2068

-የሜትር ታክሲዎች ስለሚከፍሉት የግብር አይነት ማብራሪያ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2069

-ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በፓርላማ ንግግራቸው የኢኮኖሚ ዕድገትን በተመለከተ ያቀረቡትን መረጃ ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2070

-በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚንስትሩ በፈረንሳይ ኢንተርኔት እንዲቋረጥ ስለመወሰኑ የተናገሩትን መረጃ አጣርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2072

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::