ኢንተርኔት በፈረንሳይ እንዲቋረጥ ተደርጓል?

pm-abiy-ahmeds-claim-about-the-internet-restriction-in-france-is-incorrect-ኢንተርኔት

ሰኔ 29፣ 2015

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ በፈረንሳይ ኢንተርኔት እንዲቋረጥ ስለመወሰኑ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚዲያን በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት ንግግራቸውበኢትዮጵያ ብቻ አይደለም፤ ሰሞኑን ሰምታችኋል ፈረንሳይ ችግር ነበር፣ በአውሮፓ ምድር በፈረንሳይ አገር ለመጀመሪያ ጊዜ ኢንተርኔት እንዲቋረጥ ተወስኗል። የአፍሪካ የተለመደ ነው…” ሲሉ ተደምጠዋል።

ሆኖም ኢትዮዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንሳይ አገር ለመጀመሪያ ጊዜ ኢንተርኔት እንዲቋረጥ ተወስኗል በማለት የተናገሩት የተሳሳተ መሆኑን አረጋግጧል።

ነገሩ እንዲህ ነበር:

በፈረንሳይ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ስምንና አርማ በመጠቀም የተጻፈ አንድ ደብዳቤ ባሳለፍነው ዕሁድ በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጨ። ደብዳቤው በሀገሪቱ ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በኢንተርኔት ላይ እቀባ መጣሉን የሚገልጽ ነበር።

ሆኖም የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ወዲያኑ ባወጣው መግለጫ የተሰራጨው ደብዳቤም ሆነ በኢንተርኔት ላይ እቀባ እንዲጣል ውሳኔ ተላልፏል የሚለው መረጃ ሀሠተኛ መሆኑን አስታውቋል።

ኤፒን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ የመረጃ አጣሪ ተቋማትም የመረጃውን ሀሠተኝነት በተመለከተ ዘገባሰርተዋል።

በተጨማሪም ፕሬዝደንት ማክሮን ከአንድ ቀን በፊት ከከንቲባዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በኢንተርኔት ላይ እቀባ አለመደረጉን አረጋግጠዋል። ሆኖም ነገሮች ሲረጋጉ ኢንተርኔትን ማቋረጥን የተመለከቱ ደንቦች ሊወጡ ይችላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::