ሜታ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች ላይ ይሰሩ የነበሩ በርካታ ሰራተኞቹን እንደቀነሰ ታውቋል

Friday roundup

ሚያዝያ 20፣ 2015

1. የህንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁሉም የሀገሪቱ ክልሎችና ግዛቶች የጥላቻ ንግግሮችን እንዲመዘግቡ ከአመትበፊት ያሳለፈው ውሳኔ እንዲራዘም ማድረጉን ሚዲያዎች ዘግበዋል። ፍርድ ቤቱ ክስ ያልቀረበባቸው የጥላቻንግግሮችም እንዲመዘገቡ ማዘዙ ተገልጿል። በተጨማሪም ክልሎችና ግዛቶች ይህን ስራ የሚከውን ባለሙያእንዲመዱቡ ያዘዘ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች የጥላቻ ንግግሮችን የሚያነሱበትን አፈጻጸምየሚያሳይ መመሪያ እንዲወጣም ማዘዙ ተግለጿል። ፍርድ ቤቱ ይህ ትዕዛዝ የሰጠው በተለይም የሀገሪቱንየሀይማኖቶችን መስተጋግብር ጤንነት ለመጠበቅ መሆኑን አስታውቋል። 

2. ትዊተር መመሪያዎቹንና ፖሊሲዎቹን በመጣስ እይታቸው እንዲቀንስ የሚደረጉ ይዘቶችን ተከታዮች እንዲለዩየሚጠቁም ማሳሳቢያ መጠቀም ጀመረ። በዚህም እይታቸው እንዲቀንስ የተደረጉ ይዘቶች የሚሸፈኑ ሲሆንበሽፋኑ ላይእይታው እንዲቀንስ የተደረገ” (Visible limited የሚል ጽሁፍ እንዲነበብ ይደረጋል። ይዘቱ ለምንእርምጃ እንደተወሰደበት የሚያስረዳ አረፍተ ነገርም አብሮ የሚያያዝ ይሆናል። 

3. ሜታ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ አትኩረው ይሰሩ የነበሩ በርካታ ሰራተኞችንመቀንሱን በቴክኖሎጅ ዙሪያ የሚዘግበው ዘቨርጅ ድረገጽ ዘግቧል። በፌስቡክና በኢንስታግራም የሚሰራጩሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች ላይ አትኩሮ ይሰራ ከነበረውና 50 ሰራተኞች ካሉት የስራ ክፍል አብዛኞቹመቀነሳቸውን ነው ድረገጹ የዘገበው። ሜታ 10,000 ገደማ ሰራተኞችን እንደሚቀንስ የኩባንያው ዋና ስራአስፈጻሚ ማርክ ዙከንበርግ ከወራት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል። 

✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

በሰኞ መልዕክታችን በቀልድ መልክ ከሚቀርቡ የጥላቻ ንግግሮችን አንጻር ማድረግ ስላለብን እርምጃዎችጽሁፍ በአፋን ኦሮሞ አስነብበናል

https://t.me/ethiopiacheck/1975

እንዲሁም ከአሜሪካ ጉዞ ጋር የተገናኘ የተሳሳተ መረጃን በተመለከተ ማጣራት አድርገናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1978

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትን ከክልሉ ስርዐተ ትምህርት ማስወጣቱን የሚገልጹመረጃዎች የተሳሳቱ መረጃዎችን ፈትሸን በአማረኛና በትግረኛ ቋንቋዎች አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1981

https://t.me/ethiopiacheck/1982

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::