በዛራ ሚዲያ ኔትወርክ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ ማሳሰቢያ

ሚያዝያ 7፣ 2018
/ኢትዮጵያ ቼክ/ – በዛራ ሚዲያ ኔትወርክ ስም እና ምስል የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ የተለያዩ መረጃዎች እያጋራ መሆኑን ተመልክተናል። ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ ባደረገው ማጣራት አንዳንድ ሀሰተኛ አካውንቶች በሚዲያ ተቋሙ ስም መከፈታቸውን አረጋግጧል።
የሚድያው መስራች ጋዜጠኛ ስታሊን ሀ/ስላሴ የሚዲያ ተቋሙ ትክክለኛ ገፁ ከ160 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ይህ አካውንት እንደሆነ ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል: https://www.facebook.com/share/18guNMycpg/
ተመሳሳይ ምስል እና ስም ያለው እና ከ26 ሺህ በላይ ያለው ይህ የፌስቡክ ገፅ የሱ ገፅ እንዳልሆነ አረጋግጧል።
የታዋቂ ግለሰቦችን እና ተቋማትን ስም እና ምስል (አርማ) በመጠቀም የሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትሰስር ገፆች እና አካውንቶች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ።
በተጨማሪ ሀሰተኛ እና ተመሳስለው የሚከፈቱ አካውንቶችን፣ ገፆችን እና ቻናሎችን ለመለየት የሚረዱን ጠቋሚ ምልክቶችን ለማየት ይህን በኢትዮጵያ ቼክ የተዘጋጀ አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ። https://t.me/ethiopiacheck/1344
ኢትዮጵያ ቼክ
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::





