ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው እንደተሾሙ በመግለፅ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

ታህሳስ 13፣ 2018
ካሳለፍነው ሳምንት ወዲህ በርካታ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እና አካውንቶች ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው እንደተሾሙ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።
እነዚህ ገፆች እና አካውንቶች ምንጫቸው ከየት እንደሆነ ባይጠቅሱም ያጋሯቸው መረጃዎች በርካታ ግብረ-መልስ ሲያገኙ ተመልክተናል።
የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲሁም የህወሓት የፖሊት ቢሮ አባል የነበሩት ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂምም ሆነ የከተማው መስተዳድር ስለተወራው ሹመት እስካሁን በሚድያዎች ወይም በኦፊሴላዊ መንገዶች በኩል ያሉት ነገር የሌለ ሲሆን በነበረው የአሰራር ልምድ ምክትል ከንቲባም ሆነ ሀላፊ ሹመት ሲያገኝ ይፋ ይደረጋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀፍታይ ገብረ እግዚአብሔርን በተጨማሪ ያነጋገረ ሲሆን መረጃው ‘የተሳሳተ ነው’ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።
ምንጫቸው የማይታወቅ መረጃዎችን አምኖ ባለመቀበል እና ለሌሎች መልሶ ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።
ኢትዮጵያ ቼክ
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
