በሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ህልፈት ዙርያ ዋልታ የተጠቀመው አሳሳች ምስል

ሀምሌ 14፣ 2016 ዓ.ም
በትናንትናው እለት ህይወታቸው ባለፈው የ ‘ዊ ቢዩልድ’ ወይም በቀድሞው ስሙ ‘ሳሊኒ ኮንስትራክሽን’ መስራች እና ባለቤት በሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ህልፈት ዙርያ ዋልታ በሰራው ዘገባ ላይ የተጠቀመው ምስል አሳሳች መሆኑን ተመልክተናል።
በዜና ዘገባው ላይ ምስላቸው የተቀመጠው የአሁኑ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ፒየትሮ ሳሊኒ ናቸው። ፒየትሮ ሳሊኒ የሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ልጅ ናቸው።
ሳሊኒ እንደ ህዳሴ ግድብ፣ የጊቤ ሀይል ማመንጫ ግድቦች እንዲሁም ሌሎች ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ለበርካታ አስርት አመታት የተሳተፈ ግዙፍ የጣልያን የግንባታ ተቋም ነው።
ሚድያዎች የሚጠቀሟቸውን ምስሎች፣ ቪድዮዎች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች ለህዝብ ከማድረሳቸው በፊት ማጣራት (fact check) በማድረግ ለህዝቡ የጠራ መረጃ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
