እነዚህ ምስሎች ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ሰሞኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ ያረጉትን ንግግር እና የተመድ ዋና ፀሐፊ ምላሽ አያሳይም

መስከረም 17፣ 2019

/ኢትዮጵያ ቼክ/ — ባለፉት ጥቂት ቀናት ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ኒው ዮርክ፣ አሜሪካ እየተካሄደ ባለው የ81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተሰናባቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር አደረጉ የተባለው ቃላት ምልልስ ቪዲዮ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።

ይህ ቪዲዮ በዚህ ሳምንት በርካታ ተከታዮች ባላቸው የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እየተጋራ እና በርከት ያሉ መስተጋብሮችን እያስተናገደ ይገኛል።

ይህን ቪዲዮ መረጃ ካጋሩ መካከል Umut Cagri Sari የተባለ ኤክስ ላይ ከ10 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገፅ ይገኛል: https://x.com/umutcagrisariii/status/2104160684313383191 በዚህ አካውንት የተጋራውን ልጥፍ ወደ 91 የሚሆኑ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 14 የሚሆኑት መልስ ሰጥተውበታል።

በተመሳሳይ 1991 የተባለ ከ 1,700 በላይ ተከታዮች ያሉት የኤክስ ገፅ መረጃውን ያጋራ ሲሆን 198 የሚሆኑ የኤክስ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 32 የሚሆኑት መልስ ሰጥተውበታል። https://x.com/Meconneno/status/2104085168596070750

በተጨማሪም በርካታ የኤርትራ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች እንደሆኑ የሚጠቁሙ አካውንቶች መልዕክቱን በስፋት አሰራጭተዋል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በቪዲዮ ምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ከሰሞኑ የተደረገ ምልልስ እንዳልሆነ አረጋግጧል።

ምስልን በምልሰት በመፈለግ ባደረግነው ማጣራት ቪዲዮው ፕሬዝደንት ታዬ በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእከተኛ በነበሩበት ጊዜ መስከረም 26 2014 የተደረገ የቃላት ምልልስ መሆኑን አረጋግጧል: https://youtu.be/Sy3zq422Gj4?si=adIWo17TibZQlq_d

በዚህ ሰሞን ፕሬዝዳንት ታዬ አስቀስላሴ ኒው ዮርክ ያደረጉትን ንግግር ቪዲዮ በተለያዩ ተቋማት ገፅ ላይ ማግኘት ይቻላል: https://youtu.be/d0ekOP-ts_Y?si=wDwm2xg84qslLGMs

በዚህም መሰረት ስለዚህ እነዚህ ቪዲዮች ከአውድ ውጭ የተጋሩ እና አሳሳች መሆናቸውን አረጋግጠናል።

በተለይ በግጭት ወቅት ከአውድ ውጭ እና አሳሳች በሆነ መልኩ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን እንዲሁም ከማመናችን በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::