“በወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለቀረበ ጥያቄ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠ መልስ እንደሆነ በመጥቀስ እየተጋራ የሚገኝ ደብዳቤ ሀሰተኛ ነው” —አቶ አገኘሁ ተሻገር

ግንቦት 12፣ 2018

/ኢትዮጵያ ቼክ/- የፌዴሬሽን ምክር ቤት በወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠዉን መልስ የያዘ እንደሆነ የተገለጸ ደብዳቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ይገኛል።

ይህ ደብዳቤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ስም የሰፈረበት ሲሆን ግንቦት 12፣ 2018 ወጪ የተደረገ እንደሆነም በደብዳቤዉ ተጠቅሷል።

የደብዳቤዉ ዋና ይዘት ደግሞ ‘በወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የቀረበዉ የማንነትና ራስ ገዝነት አስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ ተቀባይነት የሌለዉ እና ሙሉ በሙሉ ውድቅ የተደረገ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጥብቅ ያሳውቃል” የሚል ነው።

ይህን ደብዳቤ ካጋሩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘ደጀን ግራካሕሱ ሚዲያ ኔትዎርክ’ እና ‘ቤት ፅሕፈት ህወሓት ከተማ ኮረም’ የሚሉ የፌስቡክ ገጾች ይገኙበታል።

ይሁን እንጂ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በተረጋገጠ የፌስቡክ ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ ደብዳቤው ሀሰተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

አፈ ጉባዔው “የፌዴሬሽን ምክር ቤት በወልቃይት ጉዳይ ያወጣው መግለጫ በሚል በማኀበራዊ ሚዲያ የሚዟዟረው ደብዳቤ ፍጹም ሐሰትና በቅንብር ፎቶ የተሰራ መሆኑን እየገለፅኩ ይህን የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩት እነማን እንደሆኑ አጣርተን ለህግ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን” ብለዋል።

አፈ ጉባዔው በፌስቡክ ገጻቸው ያጋሩት መረጃ በዚህ ማስፈንጠሪያ ይገኛል፡

https://www.facebook.com/share/p/14h6RpnEwNE/?mibextid=wwXIfr

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::