ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአማርኛና የታሪክ ትምህርት ክፍሎችን ሊዘጋ ነው ስለመባሉ ያሰባሰብነው መረጃ

ሐምሌ 03፣ 2015

– “የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊና በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጆች ስር የሚገኙ ትምህርት ክፍሎችንእንዲሁም የህግና የስነ ትምህርት ኮሌጆችን እንደሚዘጋ እና መምህራኑንም ከስራ እንደሚያግድ አስታውቋልመምህራን

– “የሚባረር መምህር አይኖርምየደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት / ንጉስ ታደሰ

ባለፉት ጥቂት ቀናት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ጋር በተያያዘ በርካታ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወሩተመልክተናል። ከመረጃዎቹ መካከል ዩኒቨርስቲው የታሪክና የአማርኛ ትምህርት ክፍሎችን እንዲሁም የባህልማዕከሉንና የአፄ ዘርዓ ያቆብ የመካከለኛው ዘመን ታሪክ ጥናት ማዕከልን ለመዝጋት መወሰኑን የተመለከቱይገኙበታል።

በተጨማሪም የዩኒቨርስቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና የተፈጥሮ ሳይንስና መምህራን ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲቦርድ አስተዳደር ጽህፈት ቤት የጻፉትን የተቃውሞ ደብዳቤ እና ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ ተመልክተናል።

መምህራኑ በጻፉት ደብዳቤየደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ አመራርበልየታና በልህቀት ማዕከል ያልተካተቱ ናቸውበሚል ሰበብ በማህበራዊና በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጆች ስር የሚገኙ ትምህርት ክፍሎችን እንዲሁም የህግና የስነትምህርት ኮሌጆችን እንደሚዘጋ እና መምህራኑንም ከስራ እንደሚያግድ በመደበኛ ስብሰባ ለመምህራኑአስታውቋልየሚል ይገኝበታል። በተጨማሪም የአማርኛ ትምህርት ክፍል እና የትምህርት ክፍሉ መምህራንከሐምሌ 1 ቀን 2015 . ጀምሮ የስራ ስንብት ደብቤ እንደሚደርሳቸው መነገሩን ያስነብባል።

ጉዳዩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ ያነጋገራቸው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት / ንጉስ ታደሰውሳኔው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ሳይሆን የትምህርት ሚንስቴር ነው፤ ጉዳዩም ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲን ብቻሳይሆን ሁሉንም ዩኒቨርሲቲዎች የሚመለከተ ነውበማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

ፕሬዝደንቱ እንዳብራሩት ውሳኔው የተወሰነው ከዓመታት በፊት በቀድሞው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርትሚኒስቴር ሲሆን ዓላማውም አጠቃላይ ትምህርት ሲስጡ የቆዩ የሀገሪቱን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስንየትኩረት አቅጣጫ እንዲኖራቸው በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል።

ከውሳኔው በኋላ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥናት ማድረጉን የገለጹት / ንጉስ በዚህም የሀገሪቱን የከፍተኛትምህርት ተቋማትን በሶስት በመክፈል የትኩረት አቅጣጫ እንዲመሩ መወሰኑን ገልጸዋል።

በዚህም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የመጀመሪያ ትውልድ በመባል የሚታወቁት ስምንት የከፍተኛትምህርት ተቋማት የምርምር ዩኒቨርስቲዎች እንዲሆኑ፤ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የሁለተኛ ትውልድተብለው የሚታወቁት እንዲሁም አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅዩኒቨርሲቲ ደግሞ የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሆኑ መወሰኑን ተናግረዋል። ሌሎች የሶስተኛ ትውልድዩኒቨርሲቲ በመባል የሚታወቁት በበኩላቸው አጠቃላይ ትምህርት የሚሰጡ እንዲሆኑ መወሰኑንምአስታውሰዋል።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን ከተወሰነ በኋላ የከተማውንና የአካባቢውን ፍላጎትናግብዓት መሰረት በማድረግ አራት የትኩረት መስኮች ላይ ብቻ እንዲሰራ መወሰኑን ለዚህም ጥናትና ምክክርመደረጉን ፕሬዝደንቱ ለኢትዮጵያ ቼክ አስረድተዋል። የትኩረት መስኮቹም ኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጅ፣ ግብርና፣ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም ጤና መሆናቸውን አብራርተዋል።

የሌሎቹ የትምህርት ክፍሎች እና መምህራን የወደፊት እጣ ፈንታ

ከላይ የተጠቀሱት መምህራን በደብዳቤያቸው እና በአቋም መግለጫቸው እንዲሁም ለኢትዮጵያ ቼክእንደገለጹት በዩኒቨርሲው የትኩረት ልየታ አኳያ የሚዘጉ የትምህርት ክፍሎችና የሚባረሩ መምህራን እንደሚኖሩገልጸዋል። በደብዳቤያቸውም የአማርኛ ትምህርት ክፍልና የትምህርት ክፍሉ መምህራን ከሐምሌ 1 ቀን 2015 . ጀምሮ የስንብት ደብዳቤ እንደሚደርሳቸው መነገሩን አስነብበዋል።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት / ንጉስ ታደሰይህ መረጃ የተዛባ ነውሲሉ ለኢትዮጵያ ቼክ ተናግረዋል።የሚባረር መምህር አይኖርም፣ በልየታው ካልተካተቱ የትምህርት ክፍሎች የሆኑ መምህራ ኮመንኮርስ (common course) በመባል የሚታወቁ ትምህርቶችን በመስጠት ይቀጥላሉ። ሌሎቹ ደግሞ የትምህርት መስካቸውወደሚገኙባቸው ዩኒቨርሲቲው እንዲሸጋሸጉ ይደረጋልበማለት ተናግረዋል።

በተጨማሪም እንደ አማርኛ ያሉ በኮመንኮርስ የማይወሰዱ የትምህርት ዓይነቶችን ለማስቀጠል ከመምህራኑ ጋርመወያየታቸውን የሚገልጹት ፕሬዝደንቱ የቋንቋ ጥናት ማዕከል (Language Study Center) በማቋቋምአጫጭር ኮርሶችን እንዲሰጡ ሀሳብ ማንሳታቸውን ገልጸዋል።

ይህን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ ያነጋገራቸው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ሃላፊ / ዘውዱ ናሁሰናይ ሀሳቡመነሳቱ ገልጸው ሆኖም አብዛኛውን መምህራን ሊያስቀጥል ይችላል የሚል እምነት በብዙ መምህራን ላይአለመኖሩን አስረድተዋል። ሆኖም ማዕከሉን ለማቋቋም ሰነድ ማዘጋጀት መጀመራቸውን ገልጸው የመምህራኑዋና ፍላጎት የትምህርት ክፍሉን ህልውና ማስቀጠል መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ ጋር በተገናኘ ፕሬዝደንቱ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በተማሪዎች ተፈላጊነቱ መቀንሱን፣ ባለፉት ሶስትአመታትም ተማሪዎችን አለመቀበላቸውን የተናገሩ ሲሆን የትምህርት ክፍሉ ሃላፊ በአንጻሩ ይህ በአማርኛ ብቻሳይሆን በብዙ ትምህርት ክፍሎች የታየ መሆኑን አስረድተዋል።የትምህርት ክፍሉ ቀጣይነት መለካት ያለበትምበተማሪዎች ፍላጎት ብቻ ሳይሆን አማርኛ ቋንቋ ካለው ሀገራዊ ፋይዳ አኳያመሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ሌላው በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውና በመምህራኑም የተነሳው ጉዳይ በዩኒቨርሲቲው የሚገኘው የባህልማዕከል እና የአፄ ዘርዓ ያቆብ የመካከለኛ ዘመን የታሪክ ጥናት ማዕከል መዘጋት ነው።

ጉዳዩን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት የባህል ማዕከሉ ከዩኒቨርሲቲው የትኩረትአቅጣጫ ጋር እንዲሄድ ለማድረግ እየተሞከረ መሆኑን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በሚገኝበት ከተማ የባህልማዕከል መኖሩን ያስረዱት ፕሬዝደንቱ የዩኒቨርሲቲው የባህል ማዕከል ተመሳሳይ ስራ ከሚሰራ በሚቋቋመውየቋንንቋ ማዕከል ስር ሆኖ ጥናቶችን በማድረግ የከተማውን የባህል ማዕከል እንዲረዳ ሀሳብ መኖሩንተናግረዋል።

የአፄ ዘርዓ ያቆብ የመካከለኛ ዘመን የታሪክ ጥናት ማዕከል የሚባለው ግን ሀሠት ነው፤ እንደዚህ የሚባልማዕከል የለንምሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። / ጨምረውምእንዲህ ያለው ጉዳይ የፖለቲካ ማጣፈጫ ነውብለዋል።

ፎቶ: ፋይል

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::