ቲክቶክ ከሳህራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገሮች ለሚሰራቸው ስራዎች የመጀመሪያውን የደህንነት አማካሪ ምክር ቤት አቋቋመ

Friday roundup

ነሐሴ  17፣ 2016

1. ቲክቶክ ከሳህራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገሮች ለሚሰራቸው ስራዎች የመጀመሪያውን የደህንነት አማካሪ ምክር ቤት (Safety Advisory Council) ማቋቋሙን ቬንቸር አፍሪካ አስነብቧል። ስምንት አባላት ካሉት አማካሪ ምክርቤት መካከል ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው። አማካሪ ምክርቤቱ ቲክቶክ ቀጠናውን በተመለከተ በሚያወጣቸው ፖሊሲዎች እንዲሁም ፕላትፎርሙን ጤናማ የማድረግ እንቅስቃሴዎች ላይ የማማከር ስራ እንደሚሰራ ተገጿል።

2. በመጭው ጥቅምት ወር በሞዛምቢክ በሚደረገው ምርጫ የሚሳተፉ ፖለቲከኞች ከጥላቻ ንግግር እንዲታቀቡ አንድ የሀገሪቱ ትልቅ ሊቀጳጳስ ጥሪ ማቅረባቸውን ቫቲካን ኒውስ ዘግቧል። ሊቀጳጳስ ክላውዲዎ ዳላ ዙዋና ባቀረቡት ጥሪ ፖለቲከኞች ከተንኳሽና ከጥላቻ ንግግር ይልቅ በፖሊሲ ጉዳዮች እና በፓርቲ ማኒፌስቶ ላይ እንዲያተኩር ተማጽኖ አቅርበዋል። ሊቀጳጳሱ የተማጽኖ ጥሪውን ያቀረቡ በነገው ዕለት በይፋ ከሚጀመረው የምርጫ ቅስቀሳ ዋዜማ ላይ ሁነው ነው።

3.በዩናይትድ ኪንግደም እያሻቀበ የመጣው የጥላቻ ንግግር እና ጥላቻ ወለድ ወንጅል በእጅጉ እንዳሳሰበብው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘር መድሎ አስወጋጅ ኮሚቴ ገልጿል። ኮሚቴው ባወጣው ረዘም ያለ መግለጫ የዩናይትድ ኪንግደም ፖለቲከኞችን ጨምሮ የቀኝ ዘመም አክራሪዎች እያፋፋሙት ካሉት የጥላቻ ንግግር አንጻር ሀገሪቱ ተጨባጭ እርምጃ እንድትወስድ አሳስቧል። ዩናይትድ ኪንግደም በተለይም አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ማህበረሰቦችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ንግግር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መባባሱን የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች:

– በማህበራዊ ሚዲያ በሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች ሰለባ ላለመሆን የሚረዱ ነጥቦችን አሰንብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2422

-አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናገሩት ተብሎ የተሰራጨ መረጃን አጣርተን በአማርኛና በትግርኛ አቅርበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2419
https://t.me/ethiopiacheck/2418

-በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ስም እየተሰራጩ ያሉ ሀሰተኛ ደብዳቤዎችንም አጋልጠናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2421

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::