ይህ ምስል የአዲስ አበባ ከተማን የኮሪደር ልማት መብራቶች ያሳያል በሚል እየተሰራጨ የሚገኝ ሀሰተኛ መረጃ ነው

ይህ ምስል የአዲስ አበባ ከተማን የኮሪደር ልማት መብራቶች ያሳያል በሚል እየተሰራጨ የሚገኝ ሀሰተኛ መረጃ ነው

ነሀሴ 12፣ 2017

ከላይ በሚታየው የስክሪን ቅጂ ላይ የመንገድ መብራቶች የሚታዩባቸው ምስሎች የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት መብራቶች እንደሆኑ በመጥቀስ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ይገኛሉ።

እነዚህን ሁለት ምስሎች ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና አካውንቶች መከከል ከ34 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እና ‘ጥላዬ ያሚ’ የተሰኘ የፌስቡክ አካውንት አንዱ ሲሆን አካውንቱ ያጋራውን የተሳሳተ መረጃ 17 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው አጋርተውታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ የአዲስ አበባ ከተማን የኮሪደር ልማት መብራቶች እንደማያሳዩ አረጋግጧል። በተጨማሪም ምስሎቹ ከሰሞኑ የተነሱ ሳይሆን በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መዘዋወር ከጀመሩ አመታትን ያስቆጠሩ ናቸው።

ምስሎቹን በምልሰት በመፈለግ (reverse image search) ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት የተነሱ እንደሆነ በመጥቀስ ሲጋሩ የቆዩ መሆኑን ተመልክተናል።

ለምሳሌ ያክል የየመኑ ‘Sahafah24’ የመረጃ አውታር እኤአ መስከረም 25፣ 2019 ባጋራው መረጃ መስሎቹ የመን ውስጥ የተነሱ መሆኑን ጠቅሶ ነበር፡ https://sahafah24.com/article/12732144

በተጨማሪም ሊባኖስ፤ ሶሪያ እና ኢራቅ ምስሉ የተነሳባቸው ሀገራት ናቸው በሚል በተለያዩ ጊዜያት ስማቸው በማህበራዊ ትስስር ገጾች እና ድረ-ገጾች ሲነሳ የነበሩ ሀገራት ናቸው።

ከሌላ ቦታ ተወስደው አሳሳች እና ከአውድ ውጭ በሆነ መልኩ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛ መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::