በቱርክ በመካሄድ ላይ ባለው ፕሬዝደታዊ ምርጫ የሀሠተኛ መረጃ ስርጭ በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡ ተነገረ

ግንቦት 18፣ 2015 ዓ.ም
- በቱርክ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የሀሠተኛ መረጃ ስርጭ ከፍተኛ ተጽኖ በማሳደር ላይ መሆኑን አለም አቀፍ ሚዲያዎች በመዘገብ ላይ ናቸው። ሀሰተኛ ምስሎችና ፎቶዎች፣ የተቀናበሩ ፖስተሮች፣ ዲፕፌክና ችፕፌክ፣ ሀሰተኛ የወሲብ ቪዲዮዎች ወዘተ በስፋት መታየታቸው ተዘግቧል። የቱርኩ መረጃ አጣሪ ተቋም ተይት (Teyit) ሀሰተኛ መረጃዎች በስፋት መታየታቸውን የገለጸ ሲሆን ድርጊቱ ከሁሉም ወገን መታየቱን አስታውቋል። የቱርክ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩው ከማል ኪሊዳሮግሉ ሩሲያን ከምርጫው አንጻር የሴራ ትንታኔና ሀሰተኛ መረጃን በመፈብረክ የከሰሱ ሲሆን የገዥው ፓርቲ እጩ ኤርዶጋን በበኩላቸው ተፎካካሪያቸውን ሀሰተኛ መረጃ የሚሰራጭ ሰራዊት አሰማርቷል በማለት ሲከሱ ተደምጠዋል።
- በምስሎች ላይ አርትዖ ለማድረግ በስፋት ጥቅም በሚውለው የፎቶሾፕ መተግበሪያ ላይ ድጋፍ ሰጭ የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ ሊጨምር መሆኑን አዶቤ (Adobe) አስተውቋል። ይህ ጄኔሬቲቭ ፊል (Generative Fill) የሚል ስያሜ ያለው ድጋፍ ሰጭ የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ በጽሁፍ ትዕዛዝ ብቻ በምስሎች ላይ በቀላሉ አርትዖ ለመስራት ያስችላል ተብሏል። ቴክኖሎጅው የሀሰተኛ ምስሎችን ስርጭት ይበልጥ ያባብሳል የሚል ትችት እየቀረበበት ሲሆን አዶቤ በበኩሉ በሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅ ድጋፍ አርትዖ የተሰራባቸውን ምስሎች ለመለየት የሚያስችል ዳታ ከምስሎች ጋር እንደሚያያዝ ገልጿል። ይህንንም ለማወቅ verify.contentauthenticity.orgን መጠቀም ይቻላል ተብሏል።
- ሜታ ኩባንያ በአውሮፓ ህብረት የተጣለበትን የገንዘብ ቅጣት በመቃወም ይግባኝ እንደሚጠይቅ እና ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደው አስታውቋል፡፡ የፌስቡክ፣ ዋትሳፕ እና የኢንስታግራም ባለቤት የሆነው ሜታ በአውሮፓ ህብረት ዋና የግል መረጃዎች ተቆጣጣሪ ተቋም የግለሰቦችን መረጃ አሳልፎ ሰጥቷል ተብሎ የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት እንደተጣለበት ይታወቃል።
✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:
– በሰኞ መልዕክታችን በሰውሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት ስለሚፈበረኩ የሀሠተኛ መረጃ ይዘቶች በትግረኛ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2009
– እንዲሁም በቲክቶክ ስለሚሰራጩ የጥላቻ መልዕክቶች ትንታኔ አቅርበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/2011
-የሚዲያ አጠቃቀም ንቃትን የሚያጎለብቱ ቪዲዮዎችንም አጋርተናል :
https://t.me/ethiopiacheck/2013
https://t.me/ethiopiacheck/2012
https://t.me/ethiopiacheck/2010
– ተከታዮቻችን የሚሳተፉበት የቴሌግራም መጠየቅም አጋርተናል:
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
