አራተኛው የአፍሪካ ፋክትስ ሰሚት (Africa Facts Summit) በሴኔጋል መካሄድ ጀመረ
መስከረም 21፣ 2018
በአፍሪካ የሚገኙ መረጃ አጣሪ ተቋማትና ኤክስፐርቶችን የሚያሳትፈው አመታዊው የአፍሪካ ፋክትስ ጉባዔ በሴኔጋል ዳካር ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
ለአራተኛ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ጉባዔ በአፍሪካ የመረጃ ተአማኒነት እንዲጎለብት የሚደረገው ጥረት አካል ሲሆን የመረጃ ማጣራት (fact checking) ልምድ እንዲስፋፋ እና እንዲጎለብት ምክክሮች የሚደረጉበት እንደሚሆን ይጠበቃል።
የሀሰተኛ መረጃ ዘመቻዎችን መመርመር፣ የሰው ሰራሽ አስተዉሎት (AI) ተፅእኖ፣ የተቀናጁ አሰራር አማራጮች፣ ሀሰተኛ መረጃ በግጭት አከባቢዎች እንዲሁም አካባቢ ሁኔታን ያማከሉ መፍትሄዎች የሚሉት የጉባዔው አበይት አጀንዳዎች ናቸው።
በተጨማሪም በጉባዔው በአፍሪካ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመከላከል ረገድ ያሉ እድሎች እና ፈተናዎችን በተመለከተ ውይይቶች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባዔ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚሰሩ መረጃ አጣሪ ተቋማት እና የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ባለሙያዎች ተሳታፊ ናቸው። ኢትዮጵያ ቼክም በዚህ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በመጨረሻም ጉባዔው ለዉድድር ከቀረቡ የአመቱ የሀሰተኛ መረጃ ማጣራት ስራዎች አሸናፊዎች እውቅና እና ሽልማት በመስጠት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ ቼክ!
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::