ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራትበኢትዮጵያ ልክ እድገት ያረጋግጣል ተብሎ የተተነበየ ሀገር የለም“?

Speech made by Pm Abiy Ahmed regarding the economic growth projection of sub Saharan countries is incorrect

ሰኔ 29፣ 2015

/ሚር አብይ አህመድ ዛሬ በፓርላማ ተገኝተው ከህዝብ እንደራሴዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽበሰጡበት ወቅት የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ዳታዎችን ጠቅሰው ነበር።

/ሚሩ በዚሁ ንግግራቸው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት አምና፣ ማለትም .. 2022 6.4% እንደነበር፣ዘንድሮ ቢያንስ 6.1% እንደሚያድግ እንዲሁም በቀጣዩ አመት ተመልሶ 6.4% ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅተናግረዋል።

ይሁንና /ሚር አብይ በዚሁ ንግግራቸው ላይ Sub-Sahara (ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት) በኢትዮጵያ ልክእድገት ያረጋግጣል ተብሎ የተተነበየ ሀገር የለም፣ በአለምም ፈጣን እድገት እያመጡ ካሉ ጥቂት ሀገራት አንዷኢትዮጵያ ነችብለዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ IMF ዳታ ላይ ዳሰሳ አድርጓል።

IMF ዳታ እንደሚያመለክተው ዘንድሮ (.. 2023) ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ያሉት ከሰሀራ በታች ያሉትየአፍሪካ ሀገራት በቅደም ተከተል እነዚህ ናቸው:

1. ሴኔጋል– 8.3%

2. ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ– 6.3%

3. ርዋንዳ እና አይቬሪ ኮስት– 6.2%

4. ኢትዮጵያ እና ኒጀር– 6.1% ናቸው።

በቀጣዩ አመት ከፍ ያለ እድገት ያስመዘግባሉ የተባሉት ሀገራት ደግሞ:

1. ኒጀር– 13%

2. ሴኔጋል– 10.6%

3. ርዋንዳ– 7.5%

4. ሞዛምቢክ– 8.2%

5. አይቬሪ ኮስት– 6.6%

6. ኢትዮጵያ– 6.4% ናቸው።

ሪፖርቱን በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል: https://www.imf.org/en/Publications/REO/SSA/Issues/2023/04/14/regional-economic-outlook-for-sub-saharan-africa-april-2023

በዚህም መሰረት በጠቅላይ ሚኒስትሩበኢትዮጵያ ልክ እድገት ያረጋግጣል ተብሎ የተተነበየ ሀገር የለምየሚለው ንግግር የተሳሳተ መሆኑን ማየት ይቻላል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::