ይህ በልደታ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የተፃፈ ደብዳቤ ትክክለኛ ነው

ሐምሌ 23፣ 2016 ዓ.ም

ይህ በልደታ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የተፃፈ ደብዳቤ ወ/ሮ የትናየት ታደለ የተባሉ ግለሰብ በሶስት ምክንያቶች ከሀላፊነታቸው የተነሱ መሆኑን ይገልፃል።

ደብዳቤው ግለሰቧ የፓርቲው የወረዳ 3 የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ መሆናቸውን ይገልፅና በዲሲፕሊን፣ ከስራ ባልደረቦች ጋር ተግባብቶ ባለመስራት እንዲሁም ቲክቶክ ላይ “የምኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ፎቶ ያለው የኔ ጀግና በሚል በሙዚቃ በታጀበ ቪድዮ በመልቀቅ” ምክንያት ከስራቸው መሰናበታቸውን ይገልፃል።

ደብዳቤው ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት ሲንሸራሸር የተመለከትን ሲሆን የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችም እንድናጣራው ጥያቄ አቅርበውልናል።

ኢትዮጵያ ቼክ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ሁለት ምንጮች የደብዳቤውን ትክክለኛነት አረጋግጧል፣ ግለሰቧም ከስራቸው ከ 06/09/2016 ጀምሮ መታገዳቸውን አረጋግጧል።

ምንጮች አክለውም የስንብት ደብዳቤውን የፈረሙት የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ሀይሉ ከዚህ ከላይ ከተጠቀሰው ከወ/ሮ የትናየት ታደለ ስንብት ጋር ባልተያያዘ ጉዳይ በቅርቡ እርሳቸውም ከስራቸው እንደታገዱ ገልፀዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::