እነዚህ ምስሎች በደብረታቦር ከተማ በቅርቡ የተከሰተ ግጭትን አያሳዩም

Old Image used to show current conflict in Amhara

ነሐሴ 22፣ 2015 ዓ.ም

‘ሳልሲ አማራዋ’ የሚል ስያሜ ያለው የፌስቡክ ገጽ በደብረታቦር ከተማ መከላከያ ሰራዊት የእምነት ተቋማትን እንደምሽግ እየተጠቀመ ነው የሚል መልዕክት ማጋራቱን ተመልክተናል።

ገፁ ከመልዕክቱ ግርጌ ሁኔታውን ያሳያል ያላቸውን ፎቶዎች አያይዟል፣ ፎቶዎቹን ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም መልሰው ሲያጋሩት አስተውለናል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው የፌስቡክ ገጽ ያጋራቸው ምስሎች ቆየት ካለ ቪዲዮ የተወሰዱ ስክሪን ቅጅዎች መሆናቸውን አረጋግጧል።

የስክሪ ቅጅዎቹ የተወሰዱበት ቪዲዮ ከሁለት አመት ገደማ በፊት በፌስቡክ ተጋርቶ የነበረ ሲሆን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግ ኘት ይቻላል: https://fb.watch/mIovEwSVMK/?mibextid=Nif5oz

በአማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ የሚታወቅ ሲሆን በክልሉ አብዛኛው አካባቢ ኢንተርኔት መቋረጡ በሚዲያዎች መዘገቡ ይታወሳል።

ከዚህ ግጭት ጋር ተያይዞ በርካታ ከአውድ ውጪ እየቀረቡ ያሉ ምስሎች፣ ቪድዮዎች እና የፅሁፍ መረጃዎች እንዳሉ መመልከት የቻልን ሲሆን እነዚህን አሳሳች መረጃዎች ባለማጋራት የራሳችንን አስተዋፅኦ እናድርግ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::