ይህ ቪዲዮ በደብረማርቆስ ከተማ የተማረከ ሄሌኮፕተርን አያሳይም

old image used to show a captured airplane

ነሐሴ 23፣ 2015 ዓ.ም

ከ10 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እና ‘East times’ የሚል ስያሜ ያለው የፌስቡክ ገጽ “በዛሬው እለት የአማራ ፋኖ 3 ሄሊኮፕተሮችን ማርኳል” ከሚል ጽሁፍ ጋር አጭር ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል።

በተጋራው ቪዲዮም ‘TNA’ የሚል ጽሁፍ የሚነበብበት የተከሰከሰ ሄሊኮፕተር እንደሚታይ አስተውለናል። ቦታውም ደብረማርቆስ መሆኑ ተገልጿል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት የተጋራው ቪዲዮ የቆየ መሆኑን አረጋግጧል። በቪዲዮው የሚታየው ከ4 አመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመከስከስ አደጋ የደረሰበትን የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ (TNA) ኃ/የተ/የግል ማህበር ንብረት የሆነ የመንገደኞች ሄሌኮፕተር ነው።

አደጋ የደረሰበት ሄሌኮፕተር መንገደኞችን አሳፍሮ ወደ ጅማ የሚጓዝ እንደነበር ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ አባል የሆነበት የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ በወቅቱ በፌስቡክ ገጹ አስታውቆ ነበር።

ትክክለኛውን ቪዲዮም ዲደብሊው አማርኛ በፌስቡክ ገጹ ያጋራው ሲሆን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል: https://fb.watch/mJJxaqY_F6/?mibextid=Nif5oz

በአማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ከአውድ ውጪ እየቀረቡ ያሉ ምስሎች፣ ቪድዮዎች እና የፅሁፍ መረጃዎች እንዳሉ መመልከት የቻልን ሲሆን እነዚህን አሳሳች መረጃዎች ባለማጋራት የራሳችንን አስተዋፅኦ እናድርግ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::