“ፅሁፉ በግል አካውንት ላይ ስለተለጠፈ ቢሯችንን አይመለከትም”- የፕሬዝደንት ፅ/ቤት

Office of the president, Ethiopia response on the controversial tweet on the verified account bearing the name of president sahle-work Zewde የፕሬዝደንት ፅ/ቤት

መስከረም 25፣ 2017

በዛሬው እለት ከአንድ ሰአት በፊት የተረጋገጠ (verified የሆነ) የፕሬዝደንት ሳህለ-ወርቅ ዘውዴ የኤክስ (ትዊተር) አካውንት ላይ አንድ አነጋጋሪ ፅሁፍ ቀርቦ ነበር።

ፅሁፉ “እነ ጥላሁን ገሠሠ: ቴዲ አፍሮ: አሊ ቢራ:ማህሙድ አህመድ..ድንቅ ድምጻውያን መካከል ናቸው::”የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው:መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው”ይላል ማህሙድ “ዝምታ ነው መልሴ”ን ሲያዜም::ለአንድ ዓመት ሞከርኩት” የሚል ነው።

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን በተመለከተ የፕሬዝደንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑትን አቶ ፍቃዱ ሰቦቃን አነጋግሯል።

አቶ ፍቃዱ በሰጡት ምላሽ “የፕሬዝደንት ሳህለ-ወርቅ ኦፊሴላዊ አካውንት አለ፣ እኛ አስተያየት መስጠት የምንችለው በእሱ ዙርያ ነው። የተባለው ፅሁፍ በግል አካውንት ላይ ስለተለጠፈ ቢሯችንን አይመለከትም” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

ይህ ፅሁፍ አሁን ላይ በርካታ ግብረ መልሶችን እና አስተያየቶችን እያስተናገደ ሲሆን ኢትዮጵያ ቼክ ይህን መረጃ እስካጠናቀረበት ደቂቃ ድረስ አካውንቱ ላይ ይገኛል።

ፕሬዝደንት ሳህለ-ወርቅ ዘውዴን በቀጥታ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::