ሜታ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች ላይ ይሰሩ የነበሩ በርካታ ሰራተኞቹን እንደቀነሰ ታውቋል

ሚያዝያ 20፣ 2015
1. የህንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁሉም የሀገሪቱ ክልሎችና ግዛቶች የጥላቻ ንግግሮችን እንዲመዘግቡ ከአመትበፊት ያሳለፈው ውሳኔ እንዲራዘም ማድረጉን ሚዲያዎች ዘግበዋል። ፍርድ ቤቱ ክስ ያልቀረበባቸው የጥላቻንግግሮችም እንዲመዘገቡ ማዘዙ ተገልጿል። በተጨማሪም ክልሎችና ግዛቶች ይህን ስራ የሚከውን ባለሙያእንዲመዱቡ ያዘዘ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች የጥላቻ ንግግሮችን የሚያነሱበትን አፈጻጸምየሚያሳይ መመሪያ እንዲወጣም ማዘዙ ተግለጿል። ፍርድ ቤቱ ይህ ትዕዛዝ የሰጠው በተለይም የሀገሪቱንየሀይማኖቶችን መስተጋግብር ጤንነት ለመጠበቅ መሆኑን አስታውቋል።
2. ትዊተር መመሪያዎቹንና ፖሊሲዎቹን በመጣስ እይታቸው እንዲቀንስ የሚደረጉ ይዘቶችን ተከታዮች እንዲለዩየሚጠቁም ማሳሳቢያ መጠቀም ጀመረ። በዚህም እይታቸው እንዲቀንስ የተደረጉ ይዘቶች የሚሸፈኑ ሲሆንበሽፋኑ ላይ “እይታው እንዲቀንስ የተደረገ” (Visible limited የሚል ጽሁፍ እንዲነበብ ይደረጋል። ይዘቱ ለምንእርምጃ እንደተወሰደበት የሚያስረዳ አረፍተ ነገርም አብሮ የሚያያዝ ይሆናል።
3. ሜታ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ አትኩረው ይሰሩ የነበሩ በርካታ ሰራተኞችንመቀንሱን በቴክኖሎጅ ዙሪያ የሚዘግበው ዘቨርጅ ድረገጽ ዘግቧል። በፌስቡክና በኢንስታግራም የሚሰራጩሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች ላይ አትኩሮ ይሰራ ከነበረውና 50 ሰራተኞች ካሉት የስራ ክፍል አብዛኞቹመቀነሳቸውን ነው ድረገጹ የዘገበው። ሜታ 10,000 ገደማ ሰራተኞችን እንደሚቀንስ የኩባንያው ዋና ስራአስፈጻሚ ማርክ ዙከንበርግ ከወራት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል።
✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:
– በሰኞ መልዕክታችን በቀልድ መልክ ከሚቀርቡ የጥላቻ ንግግሮችን አንጻር ማድረግ ስላለብን እርምጃዎችጽሁፍ በአፋን ኦሮሞ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1975
– እንዲሁም ከአሜሪካ ጉዞ ጋር የተገናኘ የተሳሳተ መረጃን በተመለከተ ማጣራት አድርገናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1978
– የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትን ከክልሉ ስርዐተ ትምህርት ማስወጣቱን የሚገልጹመረጃዎች የተሳሳቱ መረጃዎችን ፈትሸን በአማረኛና በትግረኛ ቋንቋዎች አጋርተናል:
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
