ይህ ምስል ከሰሞኑ በጎንደር አለፋ ሻሁራ በፋኖ ታጣቂዎች የተማረኩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን አያሳይም!

ነሐሴ 24፣ 2016
በርከት ያሉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎረም የለበሱ ሰዎች ተሰልፈው የሚታይበት ምስል በተለያዩ ወቅቶች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘዋወር ተመልክተናል።
በአሁን ወቅትም ምስሉ በአማራ ክልል በመንግስት ሀይሎችና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተደረገ ካለው ዉጊያ ጋር ተያይዞ እየተዘዋወረ ይገኛል።
ከ22 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እና ‘የአማራ ፋኖ ጠቅላይ እዝ Official Page!’ የሚል ስም ያለው ኤክስ/ትዊተር አካውንትም ከአንድ ቀን በፊት ምስሉን ከሌሎች ምስሎች ጋር በመቀላቀል አጋርቶታል።
ምስሉ በጎንደር አለፋ ሻሁራ በፋኖ ታጣቂዎች የተማረኩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እንደሆኑ የሚጠቁም ጽሁፍም ከምስሉ ጋር አብሮ ተጋርቷል።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ምስሉ ከሰሞኑ የተነሳ እንዳለሆነ አረጋግጧል። በፋኖ ታጣቂዎች የተማረኩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትንም የሚያሳይ አይደለም።
ይህ ምስል የዛሬ ሁለት አመት አከባቢ በትግራይ ሀይሎች የተማረኩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን እንደሚያሳይ በመጥቀስ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘዋወር ነበር።
በወቅቱ ምስሉን ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ደግሞ ‘Hararage shows page’ የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል።
ገጹ ምስሉን እኤአ መስከረም 2፣ 2022 ከሌሎች ምስሎች ጋረ ያጋራው ሲሆን ልጥፉም በዘህ ማስፈንጠሪያ ይገኛል፡ https://www.facebook.com/share/p/kGSguafK7kyjC4rw/?mibextid=WC7FNe
ከአውድ ውጭ ተወስደው የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጥራት እናድርግ።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::
