በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮች ሪፖርት በማድረግ የሚያድርሱትን ጉዳት እንቀንስ

How to report the harm caused hate speech spread on social media

መስከረም 10፣ 2017 ዓ.ም

በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችመሬት ላይ ወርደው የሚያደርሱትን ዘርፈ ብዙ ጉዳትና ምስቅልቅል ብዙዎቻችን እንረዳለን።

በማህበረሰቦች መካከል አለመተማመን፣ ግጭት ብሎም የእርስ በርስ ጦርነት ይጭራል።

የንብረት ወድመት መንስዔ ይሆናል፤ የኢኮኖሚ እድገት እንዲቀጭጭም ምክንያት ይሆናል።

ብዙዎቻችንም ጉዳቱንና ምስቅልቅሉን በእራሳችንና በቤተሰቦቻችን ወይም በቅርብ በምናውቃቸው ሰዎች ደርሶ አይተናል።

ስለሆነም ይህን ለዘርፈ ብዙ ችግርና ምስቅልቅል መንስዔ የሆነ ጉዳይ ለመከላከል የራሳችን አስተዋጾ ማድረግ የውዴታ ግዴታችን ይሆናል።

በጎ አስተዋጿችን የጥላቻ ንግግርን ከማጋራት በመታቀብ እንዲሁም የሚያጋሩትን በመቃወም ሊገለጥ ይችላል።

ወይም የጥላቻ ንግግር ሰላባ የሆኑ ማህበረሰቦችና ግለሰቦች መደገፍና ከጎናቸው መቆም ሊሆን ይችላል።

ሌላኛው እና በቀላሉ ማድረግ የምንችለው ተግባር ደግሞ በየዕለቱ የማህበራዊ ሚዲያ መስተጋብራችን የምናያቸውን ጥላቻ አዘል መልዕክቶች ሪፖርት ማድረግ ነው።

እንደሚታወቀው አብዛኞቹ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ፕላትፎርሞች የጥላቻ ንግግርን በፖሊሲ ደረጃ የሚከለክሉ ሲሆን እንዲህ ያሉ ድርጊቶች ሪፖርት የሚደረጉባቸው ቀለል ያሉ ስርዐቶች አሏቸው።

እኛም የጥላቻ ንግግር ስንመለከት ሪፖርት በማድረግ የድርጊቱ አራማጆች በፕላትፎርሞቹ ቦታ እንዳይኖራቸው ማድረግና ተጽኗቸውን መቀነስ እንችላለን።

ሪፖርት ማድረግ የአንድ ጊዜ ወይም አልፎ አልፎ የምናደርገው ተግባር መሆን የለበትም። ሪፖርት በማድረግ ተፈላጊውን ውጤት ማምጣት የምንችለው ያለመታከት በየዕለቱ የምናያቸውን ጥላቻ አዘል መልዕክቶችን በዝምታ ባለማለፍ ነው።

በተጨማሪም ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ሪፖርት እንዲያደርጉ ማስተማርና ማበረታታት ሪፖርት የምናደርገው የጥላቻ ንግግር በይዘት በአስተናባሪዎች (content moderators) እይታ ውስጥ በቀላሉ እንዲገባ በእጅጉ ይረዳል።

ሪፖርት በምናደርግበት ጊዜ የጥላቻ ንግግሩ የተደረገበትን ከባቢያዊ አውድ በሚገባ ማስረዳትም ይኖርብናል። ይህም በአስተናባሪዎች አሉታዊ ይዘቱን በቀላሉ እንዲረዱትና እርምጃ እንዲወስዱ ያግዛል።

በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮች ያለመታከት ሪፖርት በማድረግ  የሚያድርሱትን ጉዳት እንቀንስ!

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::