ትዊተር ክፍያ ያልፈጸሙ ተጠቃሚዎቹን የአካውንት ትክክለኛነት ማረጋገጫ ሰማያዊ ባጆች አስወገደ

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ሚያዝያ 13፣ 2015

  1. ትዊተር ቀደም ባሉት ጊዜያት በነጻ የተሰጡ የአካውንት ትክክለኛነት ማረጋገጫ ሰማያዊ ባጆችን በትናትናው እለት ማስወገዱን አስታውቋል። ኩባንያው ሰማያዊ ባጆች በሽያጭ ብቻ ለተጠቃሚዎች እንደሚሰጡ ከወራት በፊት መግለጹ ይታወሳል። የትዊተርን እርምጃ ተከትሎ ቀደም ሲል በሰማያዊ ባጃቸው ይታወቁ የነበሩ አካውንቶች ከአገልግሎቱ ውጭ ሆነው ታይተዋል። ይህም ተመሳስለው ለሚከፈቱ ሀሠተኛ አካውንቶች በር ይከፍታል የሚል ስጋት ማሳደሩን ተመልክተናል።
  2.  የ2023 የሶኒ ዓለማአቀፍ ፎቶግራፍ ውድድር (Sony World Photography Award 2023) አሸናፊ ሽልማቱን እንደማይቀበል በሳምንቱ መጀመሪያ አስታውቋል። ጀርመናዊው የፎቶ ባለሙያ ቦሪስ ኤልዳግሰን ከሽልማቱ እራሱን ያገለለው ለውድድሩ ያቀረበው ፎቶ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) አማካኝነት የተፈበረከ መሆኑን ከገለጸ በኃላ ነው። ቦሪስ በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት የተፈበረከውን ፎቶ ለውድድር ያስገባው አወዳዳሪዎችን ለመፈተን እንዲሁም የውይይት አርዕስት እንዲሆን በማሰብ መሆኑን በግሉ ድረገጽ አስነብቧል። ቦሪስ በሶኒ ፎቶግራፍ ውድድር በነጻ ፈጠራ ዘርፍ ያሸነፈበት ሰው ሰራሽ ምስል ‘ሲዩዶሜንሺያ: ዘ ኤሌክትሪሽያን'(Pseudomnesia: The Electrician) የሚል አርዕስ ያለው ነበር።
  3. ትዊተር ይዘት ፈጣሪዎች የማስታወቂያ ገቢ የሚጋሩበትን አሰራር መጀመሩን አስታውቋል። በዚህም ፈጣሪዎቹ በበሚጋሯቸው ይዘቶች ላይ በሚሰራጩ ማስታወቂያዎች አማካኝነት የሚገኘውን ገቢ ከትዊተር ጋር የሚካፈሉ ይሆናል። አሰራሩ ለጊዜው በጃፓን፣ በአውስትራሊያ፣ ኒውዝላንድና ካናዳ ወደትግበራ መግባቱንም ትዊተር ገልጿል። ተችዎች ይህ አይነቱ አሰራር ሀሰተኛ መረጃ አሰራጮችንና ክሊክ አጥማጆችን ወደ ትዊተር ሊስብ ይችላል የሚል ስጋታቸውን ሲገልጹ ተስተውሏል።

    ✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

    – በሰኞ መልዕክታችን በቀልድ መልክ ከሚቀርቡ የጥላቻ ንግግሮችን አንጻር ማድረግ ስላለብን እርምጃዎች ጽሁፍ አስነብበናል: https://t.me/ethiopiacheck/1967

    – የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምስሎች የደቀኑት የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት ስጋት እና መለያ ዘዴዎችን የተመለከተ ጽሁፍም በአማርኛ፣ በትግርኛና በአፋን ኦሮሞ አቅርበናል:
    https://t.me/ethiopiacheck/1968
    https://t.me/ethiopiacheck/1969
    https://t.me/ethiopiacheck/1970

    – በአቶ ጌታቸው ረዳ ስም ተመሳስለው የተከፈቱ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንም አጋልጠናል:
    https://t.me/ethiopiacheck/1971

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::