የአርብ ሚዲያ ዳሰሳ፡ “የመብት ድርጅቶች በኢትዮጵያ የተስተጓጎለው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጅምር ጠየቁ”

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ሚያዚያ 27፣ 2015 ዓ.ም

  1. ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅትን (ሲፒጄ) ጨምሮ 47 የመብት ድርጅቶች በኢትዮጵያ የተስተጓጎለው ያሉት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀምር ጠይቀዋል፡፡ ድርጅቶቹ ከቀናት በፉት ለኢትዮጵያ መንግስት በጻፉ ግልጽ ደብዳቤ “ክፍት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ታማኝና ተደራሽ” የኢንተርኔት አገልግሎት የሰብዓዊ መብቶች ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን አጽኖት ሰጥተዋል። እንዲሁም ቀውስ በሚፈጠርበት ወቅት ያልተቆራረጠ የመረጃ ፍሰት ያለውን አወንታዊ አስተዋጾ አስታወሰዋል። በኢትዮጵያ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክና ዩቱብ ከተዘጉ ወራት የተቆጠረ ሲሆን በአማራ ክልል አንዳድ አንዳንድ አካካባቢዎች የዳት ኢንተርኔት አገልግሎት መስተጓጎሉ ይታወቃል።
  2. የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) መስራች አባት በመባል የሚታወቁት ዶ/ር ጆፍሪ ሂንተን እንደ ቻትጂፒቲ ያሉ ቴክኖሎጅዎች ለሀሠተኛ መረጃ ስርጭት በስፋት ሊውሉ ይችላሉ የሚል ከፈኛ ጽጋት እንዳላቸው ገልጹ። ዶ/ር ጆፍሪ ይህን የገለጹት ለዓመታት ከሰሩበት ጎግል መልቀቃቸውን በተመለከተ በኒውዮርክ ታይምስ ድረገጽ ባሰፈሩት ሃተታ ነው። በሰው ሰራሽ አስተውሎት ህንጸትና መጎልበት ያበረከቱት አስተዋጾ እንደሚጸጽታቸው ያብራሩት ዶ/ር ጆፍሪ ቴክኖሎጅው ባግባቡ ካልተገራ መጭውን ጊዜ አስፈሪ ያደርገዋል የሚል ስጋታቸውን አስነብበዋል።
  3. ብራዚል የማህበራዊ ሚዲዲያ እና የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡ ኩባንያዎች ሀሠተኛ መረጃዎችንና ሌሎች ህገወጥ ይዘቶችን እንዳያስተናግዱ የሚያስገድድ ህግ ለማጽደቅ ጫፍ መድረሷል የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ህጉ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን የመከላከል ሃላፊነትን በኩባንያዎቹ ላይ እንደሚጭን የተገለጸ ሲሆን ህጉን በሚተላለፉት ላይ ከበድ ያለ ቅጣት ይጥላል ተብሏል። ጎግልንና ፌስቡክን ጨምሮ በርከት ያሉ ኩባንያዎች ህጉ የሚጸድቅ ከሆነ ሳንሱርን ያስፋፋል፣ ነጻ የሃሳብ ፍሰትን ይገታል በሚል ተቃውሞ ማሰማታቸውም ተዘግቧል። ጎግል ህጉን በመቃዎች በድረገጹ ያወጣውን ጽሁፍ እንዲያነሳ መደረጉም ተገጿል።

✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት አኳያ ተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ያላቸውን ሚና የሚዳስ ስ ጽሁፍ በትግረኛ አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1985

– መረጃ ቲቪ በአማራ ክልል ይሰጣል ስለተባለ የክትባት ዘመቻ ያሰራጨውን መረጃ ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1987

-በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን በመግለጽ የተጋሩ መረጃዎችንም አጣርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1988

https://t.me/ethiopiacheck/1989

– የኮሚዲያን እሸቱ የፌስቡክ ገጽ መጠለፉን የሚያስውቅ መረጃም አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1990

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::