“38 የህወሃት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ” የሚል ዜና ዛሬ በስፋት ተሰራጭቷል።

“38 የህወሃት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ” የሚል ዜና ዛሬ በስፋት ተሰራጭቷል።

የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ዛሬ ለኢትዮጵያ ቼክ እንዳሳወቁት ተያዙ ተብለው በሚዲያዎች የተጠቀሱት ግለሰቦች በትግራይ ክልል የሚገኙ “ዋናዎቹን የህወሃት ሰዎች” የተመለከተ አይደለም።
ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም እንደገለጹት በሚድያ የተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች ከሳምንታት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ እና ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት በመከታተል ላይ የሚገኙ ናቸው። ከነዚህም መካከል ከሰሜን ዕዝ ጋር የሚደረገውን የሬዲዮ ግንኙነት እንዲቋረጥ ያደረጉ ይገኙበታል ብለው ለኢትዮጵያ ቼክ ተናግረዋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫም “በኢትዮ FM የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገልፀዋል” በሚል ያስተላለፈው መረጃ ሐሰት መሆኑን ጠቁሟል።
ኢትዮ FM በበኩሉ “38 የህወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገልፀዋል በሚል በተሰራጨዉ ዘገባ ላይ ያለዉ የስም ስህተት ብቻ መሆኑን እየገለጽን ይህን የተናገሩት ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ መሆናቸዉን እያሳወቅን ለተፈጠረዉ የስም ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ከዚህ ዉጭ ግን ዜናዉ የተጓደለ መረጃ የሌለዉ መሆኑንም ማሳወቅ እንወዳለን” ብሏል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::