ሜታ የሩብ አመቱን የአዋኪ ድርጊቶች ሪፖርትን ይፋ ኣደረገ

TikTok agrees to have its content moderated in Kenya

ግንቦት 4፣ 2015 ዓ.ም

  1. ሜታ የፈረንጆች 2023 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የአዋኪ ድርጊቶች ሪፖርትን (Adversarial Threats Report) ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱ በፌስቡክ በኢንስታግራም እና በዋትስአፕ የተስተዋሉ አዋኪ ድርጊቶችን የዳሰሰ ሲሆን የማጭበርበር፣ ተጽኖ የመፍጠር እንዲሁም ሀሠተኛ መረጃን የማሰራጨት ድርጊቶች በአዲስ አቀራረብ ጎላ ብለው መታየታቸውን አስነብቧል። የማጭበርበር ድርጊት ፈጻሚዎች የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጅዎችን የተጠቀሙ በማስመሰል ኢላማ የተደረጉ አካውንቶችን እንደሚያማልሉና እንደሚያደናገሩ በሪፖርቱ ተካቷል። በአንጻሩ መንግስታት በተቀናጀ ሁኔታ ተጽኖ የመፍጠር ሙከራ ስለማድረጋቸው ሪፖርቱ አስነብቧል። እንዲሁም በቅጥረኛ ኩባንያዎች አማካኝነት የሚከወኑ የሀሠተኛ መረጃ ስርጭቶች ጎላ ብለው መታየታቸው ተጠቅሷል። ሀሠተኛ አካውንቶች አዋኪ ድርጊቶችን ለመፈጸም ዋነኛ መሳሪያ መሆናቸውም ተገልጿል። ሪፖርቱ ምሳሌዎችንና የተወሰዱ እርምጃዎችንም ዘርዝሯል።

2. ጎግል በሰውሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ ምስሎችን በቀላሉ ለመለየት የሚረዳ አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀምር በሳምንቱ አጋማሽ አስታውቋል። አገልግሎቱ ወደስራ ሲገባ በሰውሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ ምስሎች ላይ “በሰውሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ” (AI Generated) የሚል ጽሁፍ ያስነብባል ተብሏል። በተጨማሪም በጎግል የሚጫኑ ምስሎችን የበለጠ ለመረዳት የሚያስችል አውድ እንደሚካተት ተገልጿል። የሚጨመረው አውድ ፎቶው ለመጀመሪያ ጊዜ በጎግል መቼና የት እንደተጫነ መረጃ ይሰጣል ተብሏል። አገልግሎቱን ለማግኘት ከምስሉ ከላይ በቀኝ በኩል የሚታዩ ሶስት ነጥቦችን መጫን ወይም ምስሉን በጎግል ሌንስ መፈለግ እንደሚገባ ተገልጿል። አገልግሎቱ በመጭዎቹ ወራት በአሜሪካ ወደስራ የሚገባ ሲሆን ቀጥሎም ለሁሉ ክፍት እንደሚሆን ጎግል አስታውቋል።

3. ትዊተር አዲስ ዋና ስራ አስፈጻሚ እንደሚሾም አስታውቋል። የትዊተር ባለቤትና በስራ ላይ ያለው የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢሉን መስክ እንዳስታወቀው አዲሷ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሚቀጥሉት ስድስት ሳምንታት ውስጥ ሀላፊነቷን ትረከባለች። ትዊተር ኢሉን መስክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ከሆነ በኃላ በፕላትፎርሙ የጥላቻ መልዕክቶች መበራከታቸውን በርከት ያሉ ባለሙያዎች ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወቃል።

✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን አስታከን ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ከሀሠተኛ መረጃ አንጻር ያለው ተዛምዶ ቃኝተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1996

– እንዲሁም ከአውድ ውጭ የተሰራጨን ፎቶ ፈትሸናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1998

– በትግራይ ክልል የኦሮምኛ ቋንቋ በትምህርት ስርዐቱ እንደሚካተት የገለጸን መረጃም አጣርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1999

https://t.me/ethiopiacheck/2000

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::