“የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ የዜጎችን ሰላም በማደፍረስ ትልቁን ድርሻ እየወሰደ ይገኛል” የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

መጋቢት 08፣2015

  1. የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ በአሁኑ ሰዓት የዜጎችን ሰላም በማደፍረስ ትልቁን ድርሻ እየወሰደ ይገኛል ብሎ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ባሳለፍነው ሳምንት ገልጿል። ባለስልጣኑ “ይህን  ተግባር ለመከላከልና የራሳችንን ብሎም የወገኖቻችንን ሰላም ለመጠበቅ የምናገኘውን መረጃ ትክክለኛነት ሳናረጋግጥ ባለማጋራት እንዲሁም የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩትን በማጋለጥ የዜግነት ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል” ብሎ በማህበራዊ ሚድያ ገፆቹ አማካኝነት መልዕክቱን አስተላልፏል።
  1. የሀላባ ዞን ፖሊስና የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በአካባቢው “የሀይማኖት ጥቃት እንደተፈጸመ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው” ብሎ ገልጿል። በአንዲት ተማሪ ላይ በፖሊስ እየተከናወነ የሚገኘው የምርመራ ጉዳይን በሚመለከት የሀይማኖት ጥቃት ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀና ሀሰተኛ መረጃ  መሆኑን የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያና የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት አስታውቆ በሀላባ ከተማ የተለያዩ ዕምነት ተከታዮች በመከባበር እና በሰላም የሚኖሩባት ከተማ እንደመሆኗ መጠን የፖሊስ እና የፍርድ ቤቱን ህግን ተከትሎ የመስራት ተግባርን እንዲሁም የማህበረሰቡን አብሮ የመኖር እሴትን በሚሸረሽር መልኩ የሚሰራጨው “ሀሰተኛ መረጃ” አግባብነት እንደሌለው ገልጿል።
  1. በ “ዲፕ ፌክ” ቅንብር የተሰሩ ቪድዮዎች በቬንዙዌላ በስፋት እየተለቀቁ እንደሆነ ተሰምቷል። እንግሊዝ ሀገር በሚገኝ አንድ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በተሰራ ሶፍትዌር አማካኝነት እየተቀናበሩ ያሉት እነዚህ ቪድዮዎች የኒኮላስ ማዱሮ አስተዳደርን የሚያሞግሱ መረጃዎችን መስራት አስችሏል፣ የሀገሪቱ መንግስትም የራሱን ገፅታ ለማጥራት በስፋት እየተጠቀመበት እንደሆነ ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል።

✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ሴቶችን ኢላማ ስላደረጉ ሀሰተኛ መረጃዎች መረጃ አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1905

– “መቐለ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው ሳምንት ስራ ይጀምራል” የሚለው ዜና የተሳሳተ መሆኑን አጣርተን በትግርኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ለተከታታዮቻችን አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1906

https://t.me/ethiopiacheck/1907

– የዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነን ስምና ምስል በመጠቀም ከቀናት በፊት ስለተከፈተ የትዊተር አካውንት መረጃ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1908

– በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ከተላከው እርዳታ ውስጥ ከፊሉ እየተሸጠ እንደሆነ የሚገልፅ መረጃን ያሳያል በተባለ ዙርያ ያገኘነውን መረጃ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1909

– አንድ መረጃ እውነት እንደሆነ አምነን እንድንቀበል እና እንድናጋራ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ምክንያቶች ቪድዮ አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1911

– በመጨረሻም፣ አታላይ ስለሆኑ ድረ-ገፆች ማንነት ጥልቅ መረጃ በትግርኛ ቋንቋ አቅርበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1912

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::