UNESCO urges tougher regulation of social media

የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ: የማህበራዊ ትስስር ድርጅቶች ላይ ቁጥጥር እንዲደረግ ‘UNESCO’ ጠየቀ

የካቲት 17፣2015

  1. የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጡ ኩባንያዎች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን እንዲቆጣጠሩ የሚያስገድድ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ዘዴ የሚዘይድ አለም ዓቀፍ ጉባይ እንዲካሄድ የተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ድርጅት (UNESCO)በሳምንቱ አጋማሽ ጥሪ አቅርቧል። የድርጅቱ ዋና ዳሬክተር አንድሬ አዙላይ ጥሪውን ያቀረቡት ኩባንያዎችን መቆጣጠር በሚቻልበት መንገድ ለመምከር በፈረንሳይ ፓሪስ በተደረገ የሁለት ቀናት ኮንፈረንስ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነበር። በኮንፈረንሱ ጋዜጠኞች፣ የህግ ባለሙያዎችና የሲቪክ ማህበራት ታድመዋል።
  2. የቱኒዚያ የኢኮኖሚና የማህበራዊ መብቶች ፎረም (Tunisian Economic and Social Rights Forum) የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ከስደተኞች አንጻር አሰምተወታል ያለውል የጥላቻ ንግግር እንደሚያወግዝ በሳምንቱ አጋማሽ አስታውቋል። ፎረሙ ፕሬዝደንት ኬይስ ሰዒድን ያወገዘው ከሰሀራ በስተደቡብ የመጡ ስደተኞችን በወንጀለኝነት እንዲሁም የስነ-ህዝብ ምጣኔን (demography) በማዛባት መክሰሳቸውን ተከትሎ ነው። የፎረሙ ቃል አቀባይ ሮመዳን ቤን አሞር በፕሬዝደንቱ ንግግር መሸማቀቃቸውን የገለጹ ሲሆን ንግግሩ ስደተኞቹ እንዲገለሉና መድሎ እንዲደርስባቸው የሚገፋ ነው ብለዋል። ቱኒዚያ ወደ አውሮፓ የሚያቀኑ አፍሪቃውያን እንደመሸጋገሪያ ከሚጠቀሙባቸው ሀገራት አንዷ መሆኗ ይታወቃል።
  3. የፌስቡክ እናት ኩባንያ ሜታ ፖሊሲዎቹኛ ደንቦችን በመጣስ ዕቀባ የሚጣልባቸው ደንበኞች ለምን ቅጣት እንደተጣለባቸው እንዲያውቁ የሚያደርግ አሰራር መጀመሩን አስታውቋል። ይህ አሰራር ተግባር ላይ የዋለው ዕቀባ የተጣለባቸውን ሰዎች ለማስተማርና ለወደፊት ተመሳሳይ የፖሊሲና የደንብ ጥሰት እንዳይፈጽሙ ለማሳወቅ መሆኑ በትናንትናው ዕለት ባስነበበው መጣጥፍ አስነብቧል። ቀለል ያሉና ያልተደጋገሙ ጥሰቶችን የሚፈጽሙ ደንበኞች የሚጣልባቸው የዕቀባ ጊዜም እንዲያጥር መደረጉን ገልጿል። ሜታ ማሻሻያውን ያደረገው ከኩባን ያው የበላይ ተመልካች ቦርድ (Oversight Board) በተሰጠው ምክረሃሳብ መሆኑንም አስታውቋል። ሜታ የፌስቡክ ፖሊሲዎችና ደንቦችን የሚጥሱ ደንበኞች እስከ 30 ቀናት ይዘት እንዳያጋሩ እቀባ የሚጥል አሰራር እንዳለው ይታወቃል።

✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን በኢንተርኔትና በዲጂታል መገናኛ ዘዴዎች ላይ የሚደረግ እቀባ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽኖ የተመለከተ ጽሁፍ በአፋን ኦሮሞ አስነብበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1860

– እንዲሁም በጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንትን አጋልጠናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1861

– ዋልታ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት የሜታ ኩባንያን ሰማያዊ ማረጋገጫ በተመለከተ ያጋራውን መረጃም አጣርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1867

– ለህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢ እንዲሆን ታስቦ የተከፈተው 8100 A የአጭር መልዕክት መቀበያ ቁጥርን የተመለከተ ማብራሪያም አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1867

– በተጨማሪም የተለያዩ የሚዲያ አጠቃቀም ንቃትን ከፍ የሚያደርጉ በቪዲዮ የተደገፉ መልዕክቶችን አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1864

https://t.me/ethiopiacheck/1865

https://t.me/ethiopiacheck/1866

https://t.me/ethiopiacheck/1868

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::