የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

UNESCO urges tougher regulation of social media

የካቲት 10፣2015

  1. አንድ የእስራኤል ኩባንያ በሀሰተኛ መረጃ ማቀናጀት እና በምርጫዎችን ማዛባት አገልግሎቶች በክፍያ በማቅረብ አገልግሎት ላይ ተሰማርቶ መገኘቱን ፎርቢድንስቶሪስ (forbiddenstories) በሚል መጠሪያ የሚንቀሳቀስ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች ጥምረት በሳምንቱ መጀመሪያ በአስነበበው የምርመራ ውጤት አጋልጧል። “ቲም ጆርጌ” (Team Jorge) የሚል ስያሜ የተሰጠውና በሕቡዕ ይንቀሳቀሳል የተባለው ይህ የሳይበር ኩባንያ ሀሰተኛ መረጃን የሚያቀናጁ ሶፍትዌሮችን እና አድቫንስድ ኢምፓክት ሚዲያ ሶሉዊሽንስ (Advanced Impact Media Solutions) የተባለ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን የሚያመርት ሶፍትዌር ለደንበኞቹ እንደሚያቀርብ ተነግሯል። በተጨማሪም አገር አቀፍ ምርጫዎችን የማዛባት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን እስካሁን በ30 ምርጫዎች ላይ መሳተፉም የምርመራ ውጤቱ አሳይቷል። ከኩባንያው ደንበኞች መካከልም የደህንነት ተቋማት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ይገኙበታል ተብሏል።ከጋርዲያን፣ ከሬዲዮ ፍራንስ፣ ከለሞንድ እና ከሌሎች እውቅ የሚዲያ ተቋማት የተውጣጡት ጋዜጠኞች ምርመራውን የሰሩት የኩባንያው ደንበኛ መስለው ከቀረቡና ሀላፊዎችን ካነጋገሩ በኃላ ነበር።
  2. በመጭው ሳምንት በናይጀሪያ ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በተገናኘ ሀሠተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ፖለቲከኞች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት Nigeria State Service) በትናንትናው ዕለት አስጠንቅቋል። አገልግሎቱ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው የናይጀሪያ ገዥ ፓርቲ ኦል ፕሮግረሲቭ ኮንግረስ (All Progressive Congress) የምርጫ ዘመቻ ዳሬክተር የናይጀሪያን ጦርና አንድ የግል ተወዳዳሪን መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ አሲረዋል በማለት መወንጀሉን ተከትሎ ነው። በናይጀሪያ የሚደረገው ምርጫ በሀሰተኛ መረጅና በጥላቻ መልዕክቶች እንዳይበረዝ በርከት ያሉ የመረጃ አጣሪ ተቋማትና የሲቪክ ድርጅቶች አበክረው እየሰሩ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልጹ ተሰምቷል።
  3. በፌስቡክና በኢንስታግራም ልጥፎች (posts) መነሳት ወይም አለመነሳትን የተመለከቱ ጉዳዩችን ላይ ውሳኔና ምክረሃሳቦችን የሚያቀርበው የሜታ የበላይ ተመልካች ቦርድ (Oversight Board) አሰራሩን ይበልጥ ለማቀላጠፍና ለማስፋት ማሻሻያዎችን ማድረጉን በያዝነው ሳምንት አስታውቋል። በዚህም አፋጣኝ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውን ልጥፎች 48 ሰዐታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለመመልከት መወሰኑን አስታውቋል። ይህም የተቀላጠፈ ውሳኔ ለመስጠት እንዲሁም በርከት ያሉ ጉዳዮችን ለመመልከት እንደሚያስችለው ገልጿል። የሜታ የበላይ ተመልካች ቦርድ መነሳት ሲኖርባቸው ያልተነሱ የጥላቻና ሌሎች አሉታዊ ይዘት ያላቸውን ልጥፎች እንዲሁም መነሳት ሳይኖርባቸው በፕላትፎርሙ አስተናባሪዎች (moderators) እንዲነሱ የተደረጉ ልጥፎችን ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥ አካል መሆኑ ይታወቃል።

በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን በኢንተርኔትና በዲጂታል መገናኛ ዘዴዎች ላይ የሚደረግ እቀባ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽኖ የተመለከተ ጽሁፍ አስነብበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1848

– እንዲሁም በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶር አለሙ ስሜና በድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ ስም ተመሳስለው የተከፈቱ የትዊተር አካውንቶችን በድጋሜ አጋልጠናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1850

https://t.me/ethiopiacheck/1853

– ቻትጂፒቲ (ChatGPT ) እያመጣቸው የሚገኙ ጥቅሞች እና ስጋቶችን የተመለከተ ጽሁፍም በአማርኛና በትግረኛ አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1855

https://t.me/ethiopiacheck/1856

– በተጨማሪም የተለያዩ የሚዲያ አጠቃቀም ንቃትን ከፍ የሚያደርጉ በቪዲዮ የተደገፉ መልዕክቶችን አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1849

https://t.me/ethiopiacheck/1851

https://t.me/ethiopiacheck/1854

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::