የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ፡ ትዊተር የሁከት ንግግር ፖሊሲው ላይ ማሻሻያ አደረገ

TikTok agrees to have its content moderated in Kenya

የካቲት፤ 24/2015 ዓ.ም

  1. ትዊተር የሁከት ንግግር ፖሊሲው (Violent Speech Policy) ላይ ማሻሻያ ማድረጉን በሳምንቱ አጋማሽ ላይ አስታውቋል። ማሻሻያው በሁከት ንግግርነት ሊፈረጁ የሚችሉ ይዘቶችን በዝርዝር አስቀምጧል። ሰዎችን ለመግደል፣ ለማሰቃየት፣ ጾታዊ ጥቃት ለማድረግ መዛት የሚያስቀጡ ይዘቶች መሆናቸው ተዘርዝሯል። እንዲሁም በግለሰቦችን ቤትና መጠለያ፣ መሰረታዊ አገልግሎት በሚሰጡ መሰረተልማቶች ላይ ጉዳት ለማድረስ መዛትም ክልክል መሆናቸው ተገልጿል። ሁከትን መቀስቀስና ማበረታታም በዝርዝሩ ተካተዋል። ፖሊሲዎቹን በሚጥሱ ደንበኞች ላይእንደየጥፋታቸው ጊዜያዊና ዘለቄታዊነት ያለው የአካውንት ዕቀባ እንደሚጣል በማሻሻያው ተገልጿል።
  2. በቱኒዚያ ከአፍሪካዊያን ፍልሰተኞች አንጻር ተደምጧል ያለውን የዘረኝነት ንግግር እንደሚያወግዝ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በሳምንቱ መጀመሪያ ባወጣው መግለጫ በአፍሪካ ህብረት የቱኒዚያ ቋሚ ተወካይን በአስቸኳይ ጠርቶ በጉዳዩ ዙሪያ ማናገሩን አስነብቧል። የቱኒዚያው ፕሬዝደንት ኬይስ ሰዒድ ከሰሀራ በስተደቡብ የመጡ ፍልሰተኞችን በወንጀለኝነት እንዲሁም የስነ-ህዝብ ምጣኔን በማዛባት የከሰሱበትን ንግግር ተከትሎ በርከት ያሉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት የውግዘት መግለጫ ማውጣታቸው ይታወቃል።
  3. በፈረንጆቹ 2022 ዓ.ም በ35 አገሮች 187 የኢንተኔት ዕቀባና ማስተጓጎል ድርጊቶችን መመዝገቡን አክሰስናው (Access Now) የተሰኘው በጉዳዩ ላይ የሚሰራ አለም አቀፍ ተቋም በሳምንቱ መጀመሪያ ባወጣው ሪፖርት አስነብቧል። ይህም ተቋሙና አጋሮች እንዲህ ያሉ ድርጊቶችን መመዝገብ ጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛው መሆኑ ተገልጿል። የኢንተርኔት ዕቀባውና ማስተጓጎሉ በተለይም ሰዎች የበለጠ መረጃ በሚፈልጉባቸው የአለመረጋጋት፣ የጦርነት፣ የሰብዓዊ ቀውሶች፣ ወዘተ በተከሰቱባቸው ወቅቶች መሆኑ በሪፖርቱ ተመልክቷል። አለመረጋጋቶች በሚኖሩባቸው ጊዜያት በመገናኛ ዘዴዎች ላይ የሚደረግ ዕቀባና ማስተጓጎል ለሀሠተኛ መረጃ፣ ለሴራ ትንተና እንዲሁም ለአሉባልታ ስርጭት ገፊ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
  • በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን በድረ-ገጾችና በማህበራዊ ሚዲያ የምናገኛቸውን መረጃዎች ትክ ክለኛነት ለማወቅ የሚረዱ ነጥቦችን በትግረኛ አስነብበናል: https://t.me/ethiopiacheck/1875

– እንዲሁም በሳምንቱ መጀመሪያ በአዲስ አበባ ሰማይ ስለታዩ ጄቶች መረጃ አቅርበናል: https://t.me/ethiopiacheck/1878

– ኢትዮ-አሜሪካን ዴቨለፕመንት ካውንስል በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጉባዔ ዙርያ ያሰራጨውን መረጃም አጣርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1881

https://t.me/ethiopiacheck/1882

– “ለአንድ ሀሰተኛ መረጃ በስፋት መሰራጨት ምን ምክንያት ሊሆን ይችላል?” በሚል የህዝብ መጠየቅ ያጋራን ሲሆን ውጤቱንም ተንትነናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1876

https://t.me/ethiopiacheck/1883

https://t.me/ethiopiacheck/1885

https://t.me/ethiopiacheck/1886

–  በተጨማሪም የተለያዩ የሚዲያ አጠቃቀም ንቃትን ከፍ የሚያደርጉ በቪዲዮ የተደገፉ መልዕክቶችን አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1877

https://t.me/ethiopiacheck/1879

https://t.me/ethiopiacheck/1880

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::