የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ እንደታሰሩ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

false information claiming that ex governor of national bank of ethiopia Dr Yinager Dessie is arrested

ሚያዝያ 02፣ 2015

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የነበሩት ዶ/ር ይናገር ደሴ እንደታሰሩ የሚገልፁ መረጃዎች ከዛሬ ሚያዝያ 2/2015 ጠዋት ጀምሮ በማህበራዊ ሚድያ፣ በተለይ ፌስቡክ ላይ ሲሰራጭ እንደነበር ማየት ችለናል።

እነዚህ መረጃዎች ዶ/ር ይናገር “በሙስና ወንጀል” ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የገለፁ ሲሆን በርካታ ሰዎችም በዚህ ዙርያ አስተያየት ሲሰጡ እና መልሰው ሲያጋሩ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ ይህን መረጃ በቀጥታ ዶ/ር ይናገርን በማናገር ማጣራት የቻለ ሲሆን “ውሸት ነው፣ እንዲህ አይነት መረጃ እንደተሰራጨ እንኳን እኔ መረጃው አልነበረኝም” በማለት መልስ ሰጥተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የፌደራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነቶችን መረጃ የጠየቅን ሲሆን ይህ መረጃ እንደሌላቸው ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቀዋል።

ዶ/ር ይናገር ከአምስት አመት በፊት የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው ተሹመው ለ13 አመት በብሔራዊ ባንክ ገዢነት ያገለገሉትን አቶ ተክለወልድ አጥናፉን ተክተው ነበር። ይሁንና ጥር 2015 ላይ ዶ/ር ይናገር በአቶ ማሞ ምክረቱ ተተክተዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::