በአማራ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ “ውሸት ነው” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

false information circulating about the state of emergency in Amhara

ሚያዚያ 25፣ 2015 ዓ.ም

‘Finfinnee Free Post’ የሚል ስም እና ከ294 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ “በአማራ ክልል ለሶስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል” የሚል መረጃ አጋርቷል።

ይህን በሰበር ዜና መልኩ የቀረበ መረጃ ከ50 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን ከ60 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ሀሳብ እና እስትያየታቸዉን ሰጥተዉበታል።

ይህ መረጃ ከ‘Finfinnee Free Post’ ፌስቡክ ገጽ በተጨማሪ በርከት ባሉ የፌስቡክ አካዉንቶች እና ገጾች መጋራቱንም ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ መረጃዉን በተመለከተ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህን የጠየቀ ሲሆን እርሳቸዉም መረጃው “ውሸት ነው” ብለዋል።

በሰበር መልክ የሚቀርቡ አጠራጣሪ መረጃዎች ለሀሰተኛ እና የተሳሳቱ መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ጥንቃቄ እና ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::