ፋክቲፋይ ኢትዮጵያ ይፋ ያደረገው የሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮች ስርጭት መጠን በኢትዮጵያ

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

መጋቢት 29፣ 2015

1. በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከሚለቀቁ አስር ልጥፎች መካከል አንዱ የተሳሳተ መረጃ ወይም የጥላቻ ንግግር መሆኑን ያደረኩት ጥናት አሳይቷል ሲል ፋክቲፋይ ኢትዮጵያ የተባለ ተቋም ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ዘግቧል። ጥናቱ ፌስቡክ፣ ቴሌግራምና ትዊተርን መሰረት አድጎ በማሽን ለርኒንግ ቴክኖሎጂ የተጠና መሆኑም ተገልጿል። በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞና ትግርኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ አንድ ሚሊዮኝ ልጥፎች በጥናቱ እንደተገመገሙ የተነገረ ሲሆን ከተገመገሙ አንድ ሚሊዮን ልጥፎች መካከል 50 ሺሕ የሚሆኑት የውሸት መረጃ፣ 30 ሺሕ የሚሆኑት ሁከትን የሚቀሰቅሱና 25 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ የጥላቻ ንግግሮች ሆነው መገኘታቸው ተገልጿል።

2. ህንድ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ህጓ በትናትናው ዕለት ባደረገችው ማሻሻያ ፌስቡክ፣ ትዊተርና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የመንግስት ጉዳዮችን የተመለከቱ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን በፕላትፎርማቸው እንዳያስተናግዱ ከልክላለች። ማሻሻያው ኩባንያዎቹ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ለማጣራትም መንግስታዊ የሆኑ የመረጃ አጣሪ ተቋማትን ብቻ እንዲጠቀሙ ያስገጃል። ህጉን በማያከብሩ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እንዲሁም የቴሌኮም ኩባንያዎች ከመንግስት የሚገኙት ጥበቃ ይቋረጣል ተብሏል።

3. ቲክቶክ በፕላትፎርሙ የሚጋሩ ሀሠተኛ መረጃዎችንና መርዘኛ ንግግሮችን በተመለከተ ማሻሻያ የማያደርግ ከሆነ እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ የቬትናም መንግስት አስታውቋል። የቬትናም የሚዲያ ባለስልጣን ዳይሬክተር ኳንግ ቱ ዱ በትናትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ ቲክቶክ ሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ከመከላከል አኳያ የሚፈለግበትን ሀላፊነት እየተወጣ አይደለም ሲሉ ከሰዋል። ዳሬክተሩ ከቲክቶክ በተጨማሪ ፌስቡክንና ዩትዩብን የወቀሱ ሲሆን ቲክቶክን በተመለከተ መንግስታቸው በመጭው ግንቦት ወር ጠለቅ ያለ ምርመራ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን ከዓለም የመረጃ ማጣራት ቀን ጋር የተያያዘ መረጃ በአፋን ኦሮሞ አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1947

– እንዲሁም በሀሠተኛ መረጃዎችና በጥላቻ መልዕክቶች ስርጭት ላይ ቤንዚን ያርከፈክፍ ይሆን ተብሎ ስለተፈራው ድምጽን የማቼገን (Voice Cloning) ቴክኖሎጂ አጭር ማብራሪያ አቅርበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1951

-በአፋር ህዝቦች ፓርቲ የፌስቡክ ገፅ ላይ የተሰራጨ ሀሰተኛ መረጃንም አጣርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1952

-ድረገጾች ስንጠቀም የሚጠቅሙ ነጥቦችን ያነሳንበትን ጽሁፍ በትግረኛ አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1953

-በአማራ ክልል አንዳድ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን የተመለከተ ማብራሪያም አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/1954

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::