ከተቀረፀ ሶስት አመት ቢሞላውም ማክሰኞ በፓርላማ እንደሆነ ተደርጎ የቀረበ አሳሳች ቪድዮ

This video was shot three years ago in Mekelle

መጋቢት 22፣ 2015 ዓ.ም

“Iyoba” የሚል ስያሜ ያለውና ከ222 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት “የፓርላማው ጥያቄ” በሚል ርዕስ ስር መጋቢት 19/2015 ዓ.ም በተደረገው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበ ነው በማለት አንድ ቪዲዮ ማጋራቱን ተመልክተናል።

በቪዲዮው ላይ አንድ ግለሰብ ሕገ-መንግስቱን፣ ብልጽግና ፓርቲን፣ መፈናቀለን ወዘተ የተመለከቱ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ ይታያል።

ሆኖም ከላይ የተጠቀሰው አካውንት ያጋራው ቪዲዮ ከሶስት ዓመት በፊት የተቀረጸ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት አረጋግጧል።

ቪዲዮውም  የተወሰደው “ሕገ-መንግስትን እና ህብረ-ብሔራዊ የፌዴራሊም ስርዐትን የማዳን መድረክ” በሚል መሪ ቃል ከሶስት ዓመት በፊት በመቐለ ከተማ በተደረገ ጉባዔ ወቅት ነበር።

ጥያቄውን ያቀረቡት ግለሰብም ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የመጡና ስማቸውም አልማዝ መሆኑም በቪዲዮው ላይ ተጠቅሷል።

ሙሉው ቪዲዮ በወቅቱ በትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ የዩቱብ ቻናል የተጋራ ሲሆን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል: https://youtu.be/FZZEAEUqKb8

በቅንብር ከሚሰሩ፣ ከአውድ ውጭ ከሚቀርቡ እና አሳሳች ከሆኑ ሌሎች ምስሎች እና ቪዲዮዎች ራሳችንን በመጠበቅ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::