ሜታ ሰማያዊ ባጅን በተመረጡ አገሮች ለሽያጭ ማቅረብ ጀመረ

YouTube creators who violate guidelines can now take a class

ግንቦት 11፣ 2015 ዓ.ም

  1. ሜታ የፌስቡክና የኢንስታግራም አካውንቶች ትክክለኛነት ማረጋገጫ ሰማያዊ ባጅን በዩናይትድ ኪንግደም በሽያጭ ማማቅረብ መጀመሩን ቢቢሲ በሳምንቱ አጋማሽ ዘግቧል። ሰማያዊ ባጁ በ9.99 ፓውንድ የቀረበ ሲሆን ገዥዎች የመንግስት መታወቂያ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል። ሰማያዊ ባጁ ከዩናይትድ ኪንግደም በተጨማሪ በዩናይትድ ስቴት ስ፣ በኒውዝላንድ እና በአውስትራሊያ ለገቢያ መቅረቡንም ቢቢሲ በዘገባው ጠቅሷል። ትዊትር ሰማያዊ ባጁን ቀደም ብሎ ለሽያጭ ማቅረቡ ይታወቃል።
  1. ትዊተር ደንበኞቹ ረዘም ያለ ቪዲዮ እንዲጭኑ የሚያደረግ አሰራር መጀመሩን አስታውቋል። በአዲሱ አሰራር የአካውንት ማረጋገጫ ሰማያዊ ባጅ ያላቸው አካውንቶች እስከ 2 ሰዐት ርዝመት እንዲሁም እስከ 8 ጂቢ መጠን ያለው ቪዲዮ ማጋራት ይችላሉ ተብሏል። ትዊተር  የይዘት ፈጣሪዎች የማስታወቂያ ገቢን የሚጋሩበት አሰራርን እንደሚተገብር በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል።
  1. የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤቶችን አሉታዊ ሚና ለመቆጣጠር  የህግ ማዕቀፍ ሊዘጋጅ እንደሚገባ የኦፕንኤአይ (OpenAI) ዋና ስራ አስፈጻሚ  ሳም አልትማን ጥሪ አቅርበዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው ጥሪውን ያቀረቡት የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በተመለከተ በአሜሪካ ሴኔት የህግ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ምስክርነት በሰጡበት ወቅት ነው። የሰውሰራሽ አስተውሎትን በጎ ሚናዎች ያስረዱት አልትማን ሆኖም ቴክኖሎጂው ለሀሠተኛ መረጃ ስርጭትና ለሌሎች አሉታዊ ድርጊቶች ይውላል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል። ለዚህም የህግ ማዕቀፍና ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ እንደሚያስፈልጉ መክረዋል። ኦፕን ኤአይ የጃትጂቲፒ ፈጣሪ ተቋም መሆኑ ይታወቃል።

✅️ በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌግራም ሊንኮቻቸው:

– በሰኞ መልዕክታችን ማህበራዊ ሚዲያ ለአሉታዊ ድርጊቶች እንዴት እንደሚውልና ማድረግ ስላለብን ጥንቃቄዎች አስነብበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2003

– የበሳፋሪ ኮምን ስምና አርማ በመጠቀም የተከፈተን ሀሠተኛ የቴሌግራም ቻናል አጋልጠናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2004

– ኢቢሲ የሰራውን አሳሳች ዘገባን የሚያሳይ መረጃም አጋርተናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2005

– እንዲሁም ከአውድ ውጭ የቀረበ ምስልን አጋልጠናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2006

– ስለ ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ቪፒኤን አገልግሎት ማብራሪያ አስነብበናል:

https://t.me/ethiopiacheck/2007

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::