የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን የሚቀጥረው በራሱ ዌብሳይት ብቻ እንደሆነ አስታውቋል

ethiopian airlines

መጋቢት 14፣ 2015 ዓ.ም

እራሱን “እንቻለው ልጥገብ የአቪዬሽን ተቋም” ብሎ የሚጠራ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሰራተኞችን ለቅጥር እንዲያቀርብ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፍቃድ የሰጠው በማስመሰል ሰዎችን በማሳሳት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የከፈተውን የሂሳብ አካውንት በመጠቀም ገንዘብ በመቀበል ላይ ይገኛል ብሏል አየር መንገዱ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተጠቀሰው ድርጅትም ይሁን ከየትኛውም ሰራተኞችን ለቅጥር ከሚያቀርብ ድርጅት ጋር የስራ ስምምነት እንደሌለው አስታውቋል፡፡

አክሎም “አየር መንገዱ ሰራተኞችን የሚቀጥረው በራሱ ዌብሳይት በመግለጽ ሲሆን ከተቀጣሪዎች ምንም አይነት ክፍያ አይቀበልም፡፡ በመሆኑም ስራ ፈላጊዎች በነዚህ ድርጅቶች ሳይታለሉ ለስራ ቅጥር መረጃዎች የአየር መንገዳችንን ድረገጽ https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers
እንዲከታተሉ እናሳስባለን” ብሏል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::