የኤርትራው ፕሬዝደንት ሰጡት ተብሎ የተሰራጨ ሀሰተኛ መግለጫ

Eritreas president hasn’t commented about ASF

ሚያዝያ 02፣ 2015

“Wolkayt Tgedie Amhara Revolutio# ወልቃይትጠገዴ የአማራ ንቅናቄየሚል ስያሜ ያለው የትዊተርአካውንት በትናንትናው እለት አንድ አነጋጋሪ መረጃ አጋርቶ ነበር።

ይህ 5,400 በላይ ተከታታዮች ያሉት አካውንትታላቅ ሰበር ዜናበሚል መረጃውን ይጀምርናየኤርትራውፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ የአማራ ልዩ ኃይልን መፍረስ የለበትም ሲሉ ERI TV መግለጫ ሰጥተዋልየሚልመረጃ አጋርቷል።

አክሎምበመግለጫቸው ከአማራ ልዩ ኃይልና ሕዝብ ጎን መሆናቸውንና አስፈላጊውን የሎጅስቲክ ድጋፍእንደሚያደርጉ አስታውቀዋልይላል ይህ አሁን ላይ 520 መውደድ (like) እና 204 መልሶ ማጋራት (retweet) የተደረገ መረጃ።

ይህን መረጃ በመውሰድ (ኮፒ በማድረግ) እንደ Dessie Press Tana Media Network ወሎ ሚድያ ሴንተር(WMC)  አማራወዘተ ያሉ የፌስቡክ ገፆች እና አካውንቶችም መረጃውን በስፋት አጋርተዋል።

ይህን መረጃ ተንተርሶ ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት የኤርትራው ፕሬዝደንት ምንም አይነት ንግግር በዚህዙርያ በኤርትራ ቴሌቭዥን (Eri TV) ላይም ሆነ በሌሎች ሚድያዎች እንዳላደረጉ መመልከት ችለናል።

ከዚህም በተጨማሪ በኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር፣ በቃል አቀባይ፣ በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲወዘተላይ ባደረግነው ዳሰሳ ይህ መረጃ እንደሌለ አረጋግጠናል።

በመቀጠል ኢትዮጵያ ቼክ ያናገራቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ የኤርትራ ዲፕሎማት መረጃውየተሳሳተ መሆኑን በዛሬው እለት አሳውቀውናል።

ምንጫቸው ያልታወቀ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ባለመቀበል እንዲሁም ለሌሎች ባለማጋራት የሀሰተኛመረጃ ስርጭትን እንከላከል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::