የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምስሎች የደቀኑት የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት ስጋት እና መለያ ዘዴዎች

Disinformation threats posed by AI generated images

ሚያዝያ 09፣ 2015

ጊዜው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ነው፤ ለዚህም ከባለፈው አመት መጨረሻ ወራት ጀምሮ እንደመጣውቻትጂፒቲ አይነት ወይም እንደ ዲፕፌክ ያሉ የምንፈልገውን ሃሳብ እና የሰው ድምጽ የሚሰጡን መሳሪያዎችማሳያ ናቸው።

ሚድጀርኒ (Midjourney) ዳል (Dall-E) እንዲሁም ዲፕኤአይ በተባሉ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሳሪያዎችየሚሰሩ ምስሎች ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በሰፊው እየታዩ ነው።

አንዳንዶቹ ደግሞ መገናኛ ብዙኃን በማሳሳት ላይ ናቸው።

ማንኛውም የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት የቻለ ሰው እነዚህ መሳሪያዎች ማየት እና በቀላሉ መጠቀምይችላል።

በአጭር ደቂቃዎች ውስጥ ደግሞ በአፍታ እይታ እውነት የሚመስሉ (ከእውነት ጋር የሚጠጋጉ) ምስሎችመፍጠር ይችላል።

የኦፒያን አናላይቲክስ መስራች የሆነው ዘላለም ግዛቸውሚድጀርኒአመንጪ ዘዴዎች (creative methods) የሚጠቀም እና አሁን እየመጡ ካሉ የኤአይ መሳሪያዎች አንዱ ነው ይላል።

ይህም ባለፉት ጊዜያት ከተሰራው ዛፍ፣ ውሻ፣ ህንጻ የመሳሰሉትን እንዲለይ የሰለጠነውየቪዡዋል ሪኮግኒሽንቴክኖሎጂ በመነሳት በይበልጥ ያደጉ እና የሰለጠኑ ሆነው እንደተሰሩ ይገልጻል።

ቴክኖሎጂው ሲያድግ መገልበጥ አንችልም ወይ ብለው ተነሱ፤ ይህ ማለት ሙዝ የሚል ጽሁፍ ብንሰጠው ሙዝይስላል ወይ፣ ህንጻ ብለን ብንሰጠው ይሰጠናል ወይ የሚለው ቴክኖሎጂ ላይ ተደረሰ ማለት ነውበማለትያስረዳል።

እንደ ሚድጆርኒ ያሉ መሳሪያዎች አመንጪ ጥበብ (Generative Art) የሚፈጥሩ ሚድጆርኒ መሳል ወይምመፍጠር ስለምንፈልገው ነገር በጽሑፍ ተሰጥቶት በስእል መልክ አዘጋጅቶ የሚሰጥ ነው።

ዘላለም ይሄንን በቀላል መንገድ ሲያስረዳ አረንጓዴ ኤሊ ሳልልኝ ብሎ ለሚሰጠው፡ ሚድጀርኒ ኤአይ ኤሊ ምንእንደሆነ ያውቃል፣ ቀለም ያውቃል፤ ያንን የኮምፒዩተር ግራፊክስ ተጠቅሞ ይስለዋል ማለት ነው። አሁንማንኛውን ስነ ጥበብ ውስጥ ያሉ ቴክኒኮች ሰልጥኖ የላቀ ጽንሰሐሳብ መሳል ጀምሯል፤ ይህ በስልጠና የመጣነው ይላል።

የቪዡዋል አርት ባለሙያ የሆነው ቢንያም ወንድማገኝ የተለያዩ ምስሎች ለመስራት ሚድጀርኒ እየተጠቀሙካሉት ኢትዮጵያውያን አንዱ ነው።

ላለፉት ዘጠኝ አመታት ‘Digital Art’ ውስጥ የቆየው ቢንያም ቴክኖሎጂው የፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ሰዎችየመጀመሪያውን ሐሳብ ለማግኘት ያግዛቸዋል ብሎ ያስባል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብዛት እየተሰሩ የሚገኙት ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎች የሰው ልጅ የደረሰበትየቴክኖሎጂ ልህቀት ማሳያ ቢሆኑም ጎጂ ኃይላቸው ያሰጋናል የሚሉ በርካታ የኢንዳስትሪው ባለሙያዎች አሉ።

ይህም ቴክኖሎጂዎቹ በቀላሉ በርካታ ግለሰቦች እጅ ውስጥ የወደቁ በመሆናቸው ለሀሰተኛ መረጃ ስርጭትየመጋለጥ እድላችን ከፍ ያደርጉታል የሚል ነው።

ባለፈው የካቲት ወር ውስጥ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መታሰራቸው የሚያሳይ በሚድጀርኒየተፈበረከው ምስል ብዙዎችን አነጋግሯል።

ባለፈው ሳምንት ደግሞ የአውስትራሊያዋ ኸፕበርን ሻየር ከተማ ከንቲባ የሆኑት ብሪያን ሁድ ቻትጅፒቲን(ChatGPT) ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት እከሳለው ማለታቸው ተዘግቧል።

ቻትጅፒቲ ከንቲባውን በተመለከተ ከሚሰጣቸው መረጃዎች መካከል ከዓመታት በፊት ሙስና በመቀበል ወንጀልለእስር ተዳርገው እንደነበር የሚገልጽ የተሳሳተ መረጃ ይገኝበታል ተብሏል።

የኦፒያን አናላይቲክስ መስራቹ ዘላለም የሆነ ሐሳብ በጽሑፍ ተሰጥቷቸው ምስልን ከሚሰጡን ሚድጆርኒ እናዳል ባሻገር አሁን ከጽሑፍ ተነስቶ ድምጽ የሚያወጣ፣ የሚንቀሳቀስ ነገር ሊሰራ የሚችል የኤአይ መሳሪያእየተሰራ ነው ሲል ከኢትዮጵያ ቼክ ጋር በነበረው ቆይታ ጠቅሷል።

ብዙ ሰዓታት የሚፈጁ ነገሮች በቀላሉ ኮምፒዩተሮች እንዲሰሩዋቸው ማድረግ ተጀምሯል የሚለው ቢንያም እንደሚድጀርኒ ያሉ ቴክኖሎጂዎች የሚሰሯቸው ስራዎች ለመገናኛ ብዙኃን እንዲሁም መረጃን የማጣራት ለሚሰሩባለሙያዎች ከባድ የሚሆኑ ይመስለኛል ይላል።

ምክንያቱም በዚህ ሰአት የምናየው ነገር እንዳለ ማመን አንችልም። ለምሳሌ ዲፕፌክ የምትፈልገውን ሰው ማስተላለፍ የምትፈልገው መልእክት መተካት ይችላል። የሰው ማንነት በመተካት የተሳሳተ መረጃ ያስተላልፋልብሏል።

ይህ የሆነበት ምክንያት ማንኛውም ሰው የእያዳንዳችን መረጃ በብዛት ኢንተርኔት (ኦንላይን) ላይ ስላለው ያንንማንነት በመውሰድ የተሳሳተ መረጃ ማዘጋጀት እና ማስተላለፍ የሚችልበት ሁኔታ በመኖሩ ነው ሲል ይናገራል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁል ጊዜም ስጋቶች አሉ የሚለው የቴክኖሎጂ ባለሙያው ዘላለም በበኩሉ፤ ከሚድጆርኒ በፊትእንደ ጉግል ያሉ አብዛኛዎቹ ድረ ገጾች ከቅጂ መብት ጋር በተያያዘ የሚጠቀሟቸው ምስሎች ትክክለኛአለመሆናቸውን ይገልጻል።

እነዚህ ለማርኬቲንግ የሚጠቀሟቸው ምስሎች ሰው የሚመስሉ እንጂ ትክክለኛ ምስሎች አይደሉም፤ኣብዛኛዎቹ ኤአይ ያመነጫቸው ምስሎች ናቸው። ማህበራዊ ሚዲያ ላይም ኤአይ ያመነጫቸው ተጽእኖፈጣሪዎች አሉ። ግን በዚህ አውድ ያለ ሰው ይህን አይገነዘብም ማለት አይደለም፤ ስጋቶች እንዳሉ ይታወቃልይላል።

አብዛኛው ተጠቃሚ ለሰው ሰራሽ አስተውሎቶች እና ሌሎች የኤአይ ውጤቶች አዲስ በመሆኑ ቴክኖሎጂዎቹንአለአግባብ የመጠቀም፣ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲሰራጩ የሚያደርጉ ስራዎች ላይ ሲያውላቸው እንደሚታይኢትዮጵያ ቼክ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች ያነሳሉ።

ይህ እራሱን የቻለ አደጋ ቢኖረውም ግንዛቤ እያደገ ሲመጣ፣ መረጃ የማጣራት ስራዎች ተቀባይነት ሲያድግ እናቴክኖሎጂው ለበጎ ስራ የሚያውሉት ሰዎች ከበዙ አደጋው ይቀንሳል የሚል እምነት እንዳለው ቢንያም ይናገራል።

ቴክኖሎጂው (ሚድጀርኒ) አዲስ እንደመሆኑ መጠን አሳሳች መረጃ ከማሰራጨት ጋር በተያያዘ ብዙ ችግሮችሊፈጠሩ ይችላሉ የሚለው ዘላለም ዋናው አላማው ግን ያንን እንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል ሲል ያስረዳል።

ሚድጀርኒ እና ዳል የመሳሰሉ ጥቅም ላይ የሚውሉበት መንገድ ካየን አብዛኛው ጊዜ ኪነ ጥበቡ ላይ ነው።በግራፊክ ዲዛይን ላይ ደግሞ ትልቅ ለውጥ እያመጣ ነው፤ ስእል የማይችሉ ግን ጠንካራ ምናብ ያላቸው ሰዎችየሚያስደንቅ ምስል ለመፍጠር እየተጠቀሙበት ነው። ለበጎ ነገር እንድንጠቀመው ከተፈለገ አቅጣጫውምንድን ነው የሚለው መገንዘብ ነውየሚል እምነት እንዳለው ገልጿል።

ሰዎች በተለይ ከፖለቲከኞች ምስል ጋር በተያያዘ ለሚገጥማቸው እክል በቀጥታ ታማኝ የመረጃ ምንጭ የሆኑመገናኛ ብዙኃን በመከታተል እንዲያረጋግጡ ይመከራል።

ኤአይ ያመነጫቸው ምስሎች በመጀመርያ እይታ ትክክለኛ ሊመስሉ ስለሚችሉ ባለሙያዎች ምስሎቹ ላይበትኩረት መመልከት እንዳለብን ያስገነዝባሉ።

እርግጠኛ ካልሆንን ደግሞ የምስሉን ምንጭ ለማየት ጥረት ማድረግ ይመከራል።

ለዚህም Reverse image search Tineye እንዲሁም Yandex በመጠቀም ማረጋገጥ ይቻላል።

በዚህ ጊዜ እንደ ሚድጀርኒ እና ዳል ያሉ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚያመነጫቸው ምስሎች ትልቁክፍተታችው እጅ ላይ ስለሆነ የእጅ ምስሉን ማየትም አጋዥ ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::