ይህ “ቦረና ዞን ዝናብ ዘነበ” በሚል እየተጋራ የሚገኝ ምስል ወቅታዊ የዞኑን ሁኔታ አያሳይም

The communities in the Borena zone of the Oromia region have been affected by severe drought

የካቲት 27፣ 2015 ዓ.ም

ይህ በርከት ያሉ ከብቶች ከወንዝ ውሀ ሲጠጡ የሚያሳይ ምስል ከሰሞኑ በቦረና ዞን የዘነበዉን ዝናብ የሚያሳይ መሆኑን በመጠቀስ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲጋራ ተመልክተናል።

መረጃዉ በተለይ በፌስቡክ እና በትዊተር ላይ በስፋት እየተጋራ ያለ ሲሆን በርካታ ሰዎች በሁኔታዉ መደሰታቸዉን ሲገልጹም ተመልክተናል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገዉ ማጣራት ምስሉ የቆየ እና የዛሬ አመት አከባቢ በሚዲያዎች እንዲሁም በግለሰቦች ጥቅም ላይ ውሎ የነበረ መሆኑን ተመልክተናል፡ https://www.bbc.com/afaanoromoo/oduu-60876753

በተጨማሪም የቦረና ዞን ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ትላንት የካቲት 26፣ 2015 በፌስቡክ ገጹ ባጋራዉ መልዕክት “በዞኑ ዝናብ ዘንቧል” በሚል እየተሰራጨ የሚገኘዉ መረጃ ሀሰት መሆኑን አስታውቋል፡ https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=pfbid02uaNCW8Et5F6kLk2s7gaTAAaQn34PYJcWYGMcjZtrPC4QVdr75Y9CRSgjJ2KqhLsnl&id=100064764578380

የዞኑ አርብቶ አደሮች በድርቅ ምክንያት ለችግር መጋለጣቸዉን የጠቀሰዉ ጽ/ቤቱ ህብረተሰቡ እየተሰራጨ ባለዉ ሀሰተኛ መረጃ እንዳይሳሳት አሳስቧል።

ከአዉድ ዉጭ የሚጋሩ እና ትክክለኛነታቸዉ ያልተረጋገጠ ምስሎች ለሀሰተኛ መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ጥንቃቄ እናድርግ።

ሌሎች የተጣሩ መረጃዎችን እንዲሁም የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎትን የሚያጎለብቱ መረጃዎችን ለማግኘት የቴልግራም ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡

ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopiacheck

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::