ኢትዮ-አሜሪካን ዴቨለፕመንት ካውንስል በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጉባዔ ዙርያ ያሰራጨው የተሳሳተ መረጃ

ኢትዮ-አሜሪካን ዴቨለፕመንት ካውንስል በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጉባዔ ዙርያ ያሰራጨው የተሳሳተ መረጃ

የካቲት 22፣2015

ኢትዮ-አሜሪካን ዴቨለፕመንት ካውንስል (Ethio-American Development Council) የሚል ስም እና ከ94 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትን ጉባዔ በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ አጋርቷል።

አካውንቱ በትላንትናው እለት ባጋራው መረጃ ምክር ቤቱ ላለፉት ስድስት ወራት ስብሰባ ያለማድረጉን እና የከተማዋ ከንቲባም ትልቅ ውሳኔዎችን በካቢኔያቸው እያስወሰኑ መሆኑን ጽፏል። ይህን መረጃም ከ140 በላይ የትዊተር ተጠቃሚዎች መልሰዉ ያጋሩት (retweet ያደረጉት) ሲሆን ከ270 በላይ መውደድ (like) አግኝቷል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ እንዳረጋገጠው ሶስተኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔ ጥቅምት 04/2015 ነበር የተካሄደው።

ይህም ከስድስት ወራት በታች ሲሆን በኢትዮ-አሜሪካን ዴቨለፕመንት ካውንስል ትዊተር አካዉንት የተጋራዉን መረጃ የተሳሳተ ያደርገዋል።

ምክር ቤቱ  ጥቅምት 04/2015 ባካሄደዉ ጉባዔ የተለያዩ ሹመቶችን ማጽደቁ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ቼክ በየጊዜው የሚያጋራቸዉን የተጣሩ መረጃዎች ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን አባል ይሁኑ፡

ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopiacheck

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::